መውሊድ – ከደስታ ባሻገር ምን?

1

 

1 ሺህ 501ኛው የነብዩ መሐመድ (ሰ.ዐ.ወ) የመውሊድ በዓል በእስልምና ሃይማኖት ተከታዮች ዘንድ እየተከበረ ይገኛል።

የመውሊድ በዓል በየዓመቱ በሰደቃ፤ በአዛን፤ በዱዓ፤ ሶላት እና በተለያዩ የእምነቱ ሥርዓት ይከበራል።

የሃይማኖቱ ተከታዮች በአንድነት በመሠባሠብ፤ እርስ በእርስ በመከባበር፤ ሰላም እና ፍቅርን በመግለጥ፤ እንደ ቤተሰብ በመገናኘት በድምቀት ያሳልፉታል።

የጎንደር እስልምና ጉዳይ ምክር ቤት የሕዝብ ግንኙነት ኀላፊ ሐጅ አንዋር ቃሲም የመውሊድ በዓል የነብዩ መሐመድን መወለድ ምክንያት በማድረግ ደስታቸውን ለመግለጽ፤ ክብራቸውን ለማሳየት እና ለማስታወስ የሚከበር በዓል ነው ብለዋል።

በዓሉን የተቸገሩትን በመርዳት፤ የተራቡትን በማብላት፤ የተጠሙትን በማጠጣት እና በተለያዩ በጎ ተግባራትን በመፈጸም እንደሚከበር ገልጸዋል።

በመስጊዶች በመሠባሠብ በሰደቃ፤ በአዛን፤ በዱዓ፤ ሶላት እና ሃይማኖቱ የሚፈቅደውን የተለያዩ ሥርዓቶች በመፈጸም ይከበራል ነው ያሉት።

በነብዩ መሐመድ (ሰ.ዐ.ወ) “አንድ ሰው፤ ለአንድ ሰው” በሚለው አስተምህሮታቸው መሠረት የተቸገሩትን መርዳት ላይ ትኩረት እንደሚደረግም አንስተዋል።

በበዓል ወቅት ከሚደረገው መደጋገፍ ባሻገር በክረምት በጎ አድራጎት በመሳተፍ፤ ዓመቱን በሙሉ መልካም ተግባር በመፈጸም እና ሃይማኖት ሳይለዩ የተቸገሩትን በመርዳት ማሳለፍ ከተከታዮች የሚጠበቅ ተግባር መኾኑንም አሳስበዋል።

የነብዩ መሐመድን አስተምህሮ በመከተል ለተቸገሩ ቅድሚያ መስጠት እንደሚገባም ተናግረዋል። መውሊድ ከደስታ ባሻገር የመተባበር፣ የመረዳዳት፣ የመተሳሰብ እና የፍቅር በዓልም ነው።

#አሚኮ #መውሊድ #ኢትዮጵያ🇪🇹

#ባሕር_ዳር #ነሐሴ_19_2018_ዓ_ም

✍️ ዘጋቢ:- ያየህ ፈንቴ

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!

Previous article“ሀገራዊ ምክክሩ የሀሳብ ልዩነቶችን በምክክር የመፍታት አዲስ ልምምድ እንዲዳብር እድል ሰጥቷል”
Next articleጀማ ንጉሥ – የሐበሻው የመውሊድ መነሻ እና የዓሊሞች ማዕከል