በደብረ ብርሃን ከተማ የተገነባው የአሽከርካሪ እና ተሽከርካሪ ብቃት ማረጋገጫ አገልግሎት ማዕከል ተጠናቅቆ ወደ ሥራ ገባ።

8
በደብረ ብርሃን ከተማ የተገነባው የአሽከርካሪ እና ተሽከርካሪ ማዕከል አገልግሎት አሰጣጥን በማዘመን ረገድ ከፍተኛ አቅም ይፈጥራል።
ተቋሙ ለአካባቢው ማኅበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ እንቅስቃሴ መፋጠን ትልቅ አዎንታዊ ተጽዕኖ ያሳድራል።
የአማራ ክልል መንገድ ትራንስፖርት እና ሎጂስቲክስ ቢሮ ኀላፊ ጋሻው አወቀ (ዶ.ር) ለግንባታው 8 ሄክታር መሬት በነፃ ላቀረበው የደብረ ብርሃን ከተማ አሥተዳደር ምሥጋና አቅርበዋል።
ለማዕከሉ ግንባታ ከ108 ሚሊዮን ብር በላይ ወጭ የተደረገ ሲኾን በቀጣይ ተግባራቱን ለማሳለጥ ከአጋር አካላት ጋር ተቀናጅቶ እንደሚሠራም ገልጸዋል።
የሰሜን ሸዋ ዞን አሥተዳዳሪ መካሻ ዓለማየሁ ለተሽከርካሪ እና ለአሸከርካሪ የብቃት ማረጋገጫ መስጠት የሰውን ሕይወት እና ደኅንነት የመጠበቅ ጉዳይ መኾኑን ተናግረዋል። የትራፊክ አደጋዎችን ለመቀነስ የቅድመ መከላከል ሥራዎችን አጠናክሮ መሥራት እንደሚገባም አስገንዝበዋል።
በዘርፉ ያሉ ፈተናዎችን ለመቅረፍ ዘመናዊ ቴክኖሎጂን መጠቀም እና የባለድርሻ አካላት ቅንጅት ወሳኝ እንደኾነም ተጠቁሟል።
የኢትዮጵያ መንገዶች ባለሥልጣን በሸዋ ቀጣና ያሉ የመንገድ ፕሮጀክቶችን በፍጥነት እንዲያስጀምርም ጥሪ ቀርቧል።
የዞኑ መንገድ ትራንስፖርት እና ሎጂስቲክስ መምሪያ ኀላፊ ደጀኔ በቀለ የአገልግሎት ጊዜን በመቀነስ ቅሬታዎችን የማቅለል ሥራ መሠራቱን ገልጸዋል።
ማዕከሉ ደረጃውን የጠበቀ እና የተቀላጠፈ አሠራር በመዘርጋት የአገልግሎት ፍጥነትን ለማሳደግም ያግዛል ብለዋል።
የአገልግሎት ክፍተቶችን ሙሉ በሙሉ ለመቅረፍ የኅብረተሰቡ እና የአገልግሎት ሰጭዎች ንቁ ተሳትፎ ወሳኝ መኾኑንም ጠቁመዋል።
አዲሱ ተቋም ዘመናዊ የሎጂስቲክስ እና የትራንስፖርት ሥርዓትን በማሳለጥ እና የዞኑን ዕድገት በማፋጠን በኩል ጉልህ አስተዋጽኦ እንደሚያበረክትም ተመላክቷል።
ዘጋቢ፦ ስንታየሁ ኃይሉ
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
Previous articleየሦስት ዓመታት የተማሪና ትምህርት ቤቶች ናፍቆት ሊፈታ ይኾን?
Next articleዋግሹም ጤና ሳይንስ እና ቢዝነስ ኮሌጅ 272 የጤና ባለሙያዎችን አስመረቀ።