“ሻደይ ውበታችን ነው” የሻደይ ተጫዋቾች

21
የሻደይ ባሕላዊ የልጃገረዶች ጨዋታ በዋግ ኽምራ ብሔረሰብ አሥተዳደር ሰቆጣ ከተማ በድምቀት መከበሩን ቀጥሏል።
የሻደይ ባሕላዊ የልጃገረዶች ጨዋታ ለዋግ ቆነጃጅቶች የመድመቂያቸው ምስጢር መኾኑን ከአሚኮ ጋር ቆይታ ያደረጉት ኪሮስ ሙሉጌታ እና ብርቱካን አወጣ ተናግረዋል።
ሻደይ ራሱን የቻለ የአዘፋፈን እና የዜማ ሥርዓት ያለው መኾኑን የተናገሩት የሻደይ ተጫዋቾቹ ይህንን ባሕላዊ የልጃገረዶች ጨዋታ ጠብቆ ማቆየት ያስፈልጋል ብለዋል።
ሻደይ ለዓመት ተለያይተው የነበሩ ሁሉ የሚገናኙበት ልዩ የፍቅር በዓል እንደኾነ ያብራራችው ደግሞ ሂሩት መላሽ ናት።
በሰቆጣ ከተማ ከቆላም ከደጋውም የሚኖሩ የዋግ ቆነጃጅቶች ያለማንም ቀስቃሽ በአንድነት ተሰባስበው በጋራ የሚያዜሙት የአብሮነት በዓል እንደኾነም ሂሩት ገልጻለች።
የሻደይ በዓል በሁለተኛ ቀን ውሎው የንግድና ባዛር ግብይቶች እና በቁንጅና ውድድሮች ደምቆ ይውላል።
#ሰቆጣ #ነሐሴ 17/2018 ዓ.ም (አሚኮ)
ዘጋቢ፦ ደጀን ታምሩ
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
Previous articleየሕገ-ወጡ ቡድን አዲስ ሴራ
Next articleየሉዓላዊነታችን ህያው ጋሻ