“ኢትዮጵያ ልዩ ሀገር ናት፣ በዓለም ክፍል ያሉ ሁሉ እንዲጎበኟት እንመክራለን” የውጭ ሀገር ጎብኝዎች

4

 

የአሸንድዬ በዓል በቅዱሰ ላሊበላ በድምቀት ተከብሯል።
በበዓሉ የውጭ ሀገር ጉብኝዎች ተገኝተዋል።

በበዓሉ ላይ የተገኙት የውጭ ሀገር ጎብኝዎች የተመለከቱት የበዓል አከባበር ልዩ ስሜት እንደፈጠረባቸው ገልጸዋል።

የማኅበረሰቡ ባሕል እና የእንግዳ አቀባበል ልዩ መኾኑን ተናግረዋል። ኢትዮጵያ ልዩ ሀገር ናት፣ በዓለም ክፍል ያሉ ሁሉ እንዲጎበኟት እንመክራለን ነው ያሉት።

እንደዚህ አይነት ታሪክ አይተው እንደማያውቁም ገልጸዋል። እንደዚህ አይነት ባሕል የትም አላየንም፣ ይህ የተለየ ቦታ ነው፣ እንዲህ አይነት የተለየ ቦታም የትም አላየንም ነው ያሉት።

ከላሊበላ ኮሙዩኒኬሽን የተገኘው መረጃ እንደሚያመላክተው እዚህ ሁሉም ነገር ማራኪና ሳቢ ነው ብለዋል። ወደ ሀገራቸው ሲመለሱ የሀገራቸው ሰዎች ኢትዮጵያን በተለይም ደግሞ ላሊበላን እንዲጎበኙ እንደሚመክሩ ገልጸዋል።

Previous articleሻደይ የጥልን ግንብ የሚንድ የልጃገረዶች የደስታ ቀን ነው።
Next articleበአማራ ክልል ስምንት ትምህርት ቤቶች ሙሉ ለሙሉ ተማሪዎቻቸውን አሳልፈዋል።