ሻደይ የጥልን ግንብ የሚንድ የልጃገረዶች የደስታ ቀን ነው።

11

 

የሻደይ በዓል በዋግ ኽምራ ብሔረሰብ አሥተዳደር ሰቆጣ ከተማ እየተከበረ ይገኛል።

የዋግ ኽምራ ብሔረሰብ አሥተዳደር ምክትል አሥተዳዳሪ ሹመት ጥላሁን ሻደይ ሕዝብን በኅብረት የሚያቆም፣ የጥልን ግንብ የሚንድ፣ የልጃገረዶች የነፃነት እና የሰላም ምልክት መኾኑን ገልጸዋል።

አዲሱ ዓመትም ብሩህ ተስፋን፣ አንድነትን እና መከባበርን ይዞ እንዲመጣ የሚማጸኑበት የምሥጋና መድረክ መኾኑንም ተናግረዋል።

የዋግ ኽምራ ብሔረሰብ አሥተዳደር ባሕል፣ ቱሪዝም እና ስፖርት መምሪያ ኀላፊ ይርጋ ማርዬ በዓሉን በዩኔስኮ ለማስመዝገብ በትኩረት እየተሠራ መኾኑን ጠቁመዋል። ባሕላዊ እሴቱን ጠብቆ ለተተኪው ትውልድ ለማስተላለፍ የሁሉም አካላት የጋራ ርብርብ እንደሚያስፈልግም ተናግረዋል።

በሰቆጣ ከተማ ያለው ሰላም ሴቶች ባሕላቸውን ያለ ስጋት እንዲያከብሩ ማስቻሉን የጠቀሱት የሰቆጣ ከተማ አሥተዳደር ምክትል ከንቲባ ሙሉ ሽመልስ በበዓሉ ለታደሙ እንግዶች በዋግ ባሕል እና እሴት መሠረት ተገቢው መስተንግዶ ሊደረግላቸው እንደሚገባ አሳስበዋል።

ከአብርገሌ እና ከጋዝጊብላ ወረዳዎች የመጡት የሻደይ ተጫዋቾች ኪሮስ ሙሉጌታ እና ሂሩት መላሽ በዓሉ የውበታቸው መታያ እና የድምቀታቸው ማሳያ መስታወት መኾኑን ገልጸዋል።

በዓሉ ነገም ቀጥሎ ይከበራል። በጉጉት የሚጠበቀው የቁንጅና ውድድር እንደሚካሄድም ተገልጿል።

#አሚኮ #ሻደይ #ሰቆጣ🇪🇹

#ሰቆጣ #ነሐሴ_16_2018_ዓ_ም

ዘጋቢ፦ ደጀን ታምሩ

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!

Previous article“የሀገር መከላከያ ሠራዊት ጠላትን እየመከተ እና እያንበረከከ ጉዞውን ቀጥሏል” ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ
Next article“ኢትዮጵያ ልዩ ሀገር ናት፣ በዓለም ክፍል ያሉ ሁሉ እንዲጎበኟት እንመክራለን” የውጭ ሀገር ጎብኝዎች