
በሀገር መከላከያ ሠራዊት የልዩ ዘመቻዎች እዝ ማሠልጠኛ ማዕከል ያሠለጠናቸውን መሠረታዊ ኮማንዶዎች አስመርቋል።
የልዩ ዘመቻዎች እዝ ዋና አዛዥ ሌትናል ጄኔራል ሹማ አብደታ እዙ በአስቸጋሪ ሁኔታዎች ጭምር ሀገርን በመታደግ የሚታወቅ ነው ብለዋል።
ዛሬም ዘመኑን በዋጀ እና ኢትዮጵያን በሚመጥን መልኩ ብቁ ሠራዊት የማፍራት፤ የማሠልጠን አቅሙን የማሳደግ፤ ተዋጊ ኃይሎችን ብቻ ሳይኾን የመሪዎችን አቅም እያጎለበተ እንደሚገኝ ተናግረዋል።
በአየር ወለድ፤ በጸረ ሽብር፣ በተኩስ የእጅ በእጅ ውጊያ እና ልዩ ልዩ ዘመቻዎች የበቃ ከፍተኛ ቁጥር ያለው ሠልጣኝን ማስመረቅ መቻሉንም ገልጸዋል።
የተመረጡ ብቁ ሠልጣኞችን ለረጅም ጊዜያት የልዩ ዘመቻዎች ኮማንዶ ሥልጠናን በመስጠት በላቀ ውጤት እንዲያጠናቅቁ ማድረግ ተችሏል ነው ያሉት።
የልዩ ዘመቻ እዝ በእሳት የተፈተነ የማይቀልጥ ጠንካራ ብረት እና የጽናት ተምሳሌት ነው ያሉት ሌትናል ጄኔራል ሹማ አብደታ ዛሬም ቢኾን እንደትናንቱ ሀገር የምትሰጠውን ግዳጅ በላቀ ደረጃ ለመፈጸም ያለውን ዝግጁነት አረጋግጠዋል።
ዘጋቢ፦ ቤተልሔም ሰለሞን
#አዲስ_አበባ #ነሐሴ_16_2018_ዓ_ም
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
