
በምስራቅ ዕዝ የዞብል ክፍለ ጦር በሰከላ ወረዳ ትምህርታቸውን ለሚከታተሉ ታዳጊዎች 18 ደርዘን ደብተር እና ሁለት ፓኬት እስክፕሪቶ ድጋፍ አድርጓል ።
በምስራቅ ዕዝ ክፍለ ጦር አዛዥ ኮሎኔል ጀማል አማን ፤ የትምህርት መርጃ ቁሳቁሶችን ድጋፍ ያደረግነዉ ቤተሰቦቻቸው የገንዘብ አቅም ውስንነት ላለባቸው ተማሪዎች ነው ብለዋል።
የዛሬ ታዳጊ ተማሪዎችን መደገፉ የሰብዓዊነት ግዴታ ብቻ ሳይሆን የነገ ሀገር ተረካቢ ትውልድን የማዘጋጀት ሂደት መሆኑን አብራርተዋል ።
አዛዡ አያይዘውም ክፍለጦሩ በተሰማራበት የምዕራብ ጎጃም ወረዳዎች ሕገ መንግስታዊ ተልዕኮውን በአስተማማኝ ሁኔታ ከመወጣት ባለፈ ማኅበረሰቡን ተጠቃሚ በሚያደርጉ ልዩ ልዩ የበጎ አድራጎት ተግባራት በትጋት እየተሳተፈ መሆኑንም አስታውቀዋል።
ለተማሪዎቹ የተደረገውን ድጋፍ የተረከቡት የሰከላ ወረዳ ሴቶች ወጣቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ጽሕፈት ቤት ኀላፊ ሥራወርቅ ልመንህ፤ ሠራዊቱ በአካቢው ከተሰማራ ጊዜ ጀምሮ ካደረጋቸው የበጎ አድራጎት ተግባራት መካከል ዛሬ ለተማሪዎች የተደረገውን ጨምሮ ለአቅመ ደካማ እናቶች የገንዘብ እገዛ፣ የሱቅ ንብረታቸውን በእሳት አደጋ ላጡ ወገኖች የሥራ ማስጀመሪያ ድጋፍ እንዲሁም የመንገድ ሥራ እና ችግኝ ተከላ ዋና ዋናዎቹ መሆናቸውን አስታውሰው ሠራዊቱ ለዚህ መልካም ተግባሩም ምስጋና ይገባዋል ብለዋል። መረጃው የምስራቅ ዕዝ ነዉ።
#አሚኮ#መከላከያ_ሠራዊት #ኢትዮጵያ🇪🇹
#ባሕር_ዳር#ነሐሴ_16_2018_ዓ_ም
