“ሻደይ፣ አሸንድየ እና ሶለል የሕዝባችንን አብሮነት የሚያጠናክሩ ቅርሶቻችን ናቸው” ርእሰ መስተዳድር አረጋ ከበደ

11

 

የአማራ ክልል ርእሰ መስተዳድር አረጋ ከበደ ለሻደይ፣ አሸንድየ እና ሶለል በዓል የእንኳን አደረሳችሁ መልእክት አስተላልፈዋል።

በክልላችን ከነሐሴ ወር አጋማሽ አንስቶ በዋግኽምራ፣ በሰሜን ውሎና አካባቢው በድምቀት የሚከበሩት ሻደይ፣ አሸንድየና ሶለል ረጅም ዘመናትን የተሻገሩ የሕዝባችን መገለጫ በዓላት ናቸው፡፡

የሻደይ፣ አሸንድየ እና ሶለል በዓል በልጃገረዶችና በወጣቶች ባሕላዊ ጨዋታ ደምቀው በአደባባይ ይከበራሉ።

ልጃገረዶችና ወጣቶች በክረምቱ የለመለሙ ዕፅዋትን በመጠቀም ባሕልና እሴታቸውን የሚገልጹበት እንዲሁም ወደ ብርሃኑ የመስከረም ወር እና አዲስ ዓመት ለመሸጋገር የተስፋና የደስታ ማብሰሪያቸው ነው፡፡

ሻደይ፣ አሸንድየ እና ሶለል የሀገር ውስጥና የውጭ ሀገር ጎብኚዎችን የሚስቡ የሕዝባችን ማህበራዊ ቁርኝትና አብሮነት የሚያጠናክሩ የማይዳሰሱ ባሕላዊ ቅርሶቻችን ናቸው።

በዓላቱን ስናከብር ሕዝባችን ለዘመናት ጠብቆ ያቆያቸውን ባሕላዊ እሴቶች በማክበርና በማሳደግ፣ ለተከታዩ ትውልድ ትውፊታዊ ይዘታቸውን ጠብቀን ለማስተላለፍ በጋራ በመሥራት ሊሆን ይገባል፡፡

መልካም የሻደይ፣ አሸንድየ እና ሶለል በዓል!

Previous article“እየተመካከርን ሀገር እንገነባለን፣ ሀገር እየገነባንም እንማከራለን” ፕሬዝዳንት ታዬ አጽቀሥላሴ
Next articleየዛሬ ተማሪዎችን ማገዝ የሰብዓዊነት ግዴታ ብቻ ሳይሆን የነገ ሀገር ተረካቢዎችን የማዛጋጀት ሂደት ነው።