
የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን የምክክር ጉባኤውን የመዝጊያ ሥነ ሥርዓት አካሂዷል።
በመርሐ ግብሩ የተገኙት የቀድሞው የናይጀሪያ ፕሬዝዳንት ኦሊሴጉን ኦባሳንጆ ሀገራዊ ምክክሩ በልዩነቶች እና ባለመግባባቶች ላይ በመምከር ሀገራዊ አንድነት፤ ሰላም፤ ደኅንነት እና ዕድገት ለሁሉም ማኅበረሰብ ያለ ልዩነት ለማምጣት የተካሄደ መኾኑን ገልጸዋል።
ሰላም ሁሉም የሚፈልገው፤ ለሁሉም የሚገባ መሠረታዊ ጉዳይ ነው ያሉት ኦሊሴጉን ኦባሳንጆን ምክክር የተካሄደውም ለዚሁ ነው ብለዋል።
ሀገራዊ ምክክሩ ለኢትዮጵያ ዘላቂ ሰላም፤ መረጋጋት፤ ዕድገት እና መግባባትን እንደሚያመጣ ምኞታቸው መኾኑንም ገልጸዋል።
የተካሄደው ምክክር ለአፍሪካ ታሪካዊ ምሳሌ የሚኾን ነው ብለዋል። ኢትዮጵያ አንድ ስትኾን፤ ስትተባበር፤ ሰላም እና ልማቷን ስታረጋግጥ ካደጉት ሀገራት ተርታ መሰለፍ እንደምትችል ገልጸዋል።
ኢትዮጵያ ልዩነቶችን በአንድነት የያዘች የብሔር ብሔረሰቦች መገኛ መኾኗንም ገልጸዋል።
#አሚኮ#ሀገራዊምክክር#ኢትዮጵያ🇪🇹
#ባሕር_ዳር#ነሐሴ_16_2018_ዓ_ም
