
የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ጉባኤ የመዝጊያ ሥነ-ሥርዓት እየተካሄደ ነው። በጉባኤው የቀድሞው የኬንያ ፕሬዚዳንት ኡሁሩ ኬኒያታ ንግግር አድርገዋል።
የትኛውም የፖለቲካ ልዩነት ከሰው ልጅ ነፍስና ከሰላም እንደማይበልጥ አጽንዖት ሰጥተዋል። “ሰሜኑ ደቡቡን፣ ምሥራቁ ምዕራቡን ይፈልጋል” በማለት አንዱ ያለሌላው ሙሉ ሊኾን እንደማይችል ተናግረዋል።
ኡሁሩ ኬኒያታ የሀገራዊ የምክክር ኮሚሽኑን ጥረት እንደ ከፍተኛ የሀገር ፍቅር ተግባር አወድሰዋል። “ለአፍሪካ ችግሮች አፍሪካዊ መፍትሔ” በሚለው መርህ መሰረት ኢትዮጵያውያን ልዩነቶቻቸውን በውይይት እንዲፈቱ በማሳሰብ የኢትዮጵያ ሰላም ለመላው አፍሪካ መረጋጋትና ብልጽግና ወሳኝ ሚና እንዳለው አስገንዝበዋል።
ጆሞ ኬኒያታ የኢትዮጵያን ሰንደቅ ዓላማ የጥቁር ሕዝቦች የነጻነት ተምሳሌት አድርገው ይጠቀሙበት እንደነበርም አስታውሰዋል። የኢትዮጵያ ብዝኃነት የመለያየት ሳይኾን አብሮ የመገንባት መሰረት እንዲኾንም አስገንዝበዋል።
የኢትዮጵያ ሕዝብ ብዝኃነት የሀገሪቱ ውበትና ጥንካሬ መኾኑን በማንሳት ሀገራዊ አንድነትና ዘላቂ ሰላም እንዲጠናከር ጥሪ አቅርበዋል።
ስማቸው አጥናፍ
#Ethiopia #Ameco #NationalDialogue #PeaceBuilding
