
የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ጉባኤ የማጠቃለያ መርሐ ግብር እየተካሄደ ነው።
በማጠቃለያ መርሐ ግብሩ ንግግር ያደረጉት የሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ምክትል ዋና ኮሚሽነር ሒሩት ገብረ ስላሤ ከአንድ ወር በላይ የቆየው ሀገራዊ ምክክር ጉባኤ የነበሩትን እና ያሉትን ጥልቅ አለመግባባቶች፣ ታሪካዊ ስብራቶች እና የሀሳብ ልዩነቶች በጠብመንጃ እና በኀይል ሳይኾን በሠለጠነ መንገድ በምክክር ለመፍታት የሚያስችል አዲስ የታሪክ ምዕራፍ የከፈተ ነው ብለዋል።
በጉባኤው የሁሉም ድምጽ እንዲከበር እና እንዲደመጥ በትኩረት ተሠርቷልም ብለዋል።
ከኹሉም ኢትዮጵያውያን የተውጣጡ 4ሺህ ተመካካሪዎች የተሳተፉበት ጉባኤ መኾኑንም ገልጸዋል።
ጉባኤው ሀገራችንን ወደፊት ለማሻገር እና ዘላቂ መፍትሔ ለማምጣት በሚያስችሉ በስምንት ዋና ዋና አጀንዳዎች ላይ ሰፊ እና ጥልቅ ምክክሮች አካሂዷልም ነው ያሉት።
አጀንዳዎቹ የሀገሪቱን መሠረታዊ ችግሮች የዳሰሱ እና ለነገዋ ኢትዮጵያ መሠረት የሚጥሉ መኾናቸውንም አንስተዋል።
የጉባኤው ትልቁ ስኬት ሁሉም በአንድ ሀሳብ መስማማት ብቻ ሳይኾን በሀሳብ ልዩነት ውስጥ እርስ በእርስ መከባበርና መደማመጥ ለሀገር የተሻለ መፍትሔ በጋራ መፈለግ መቻላችን ነው ብለዋል።
አጀንዳዎቹን መነሻ በማድረግ ኢትዮጵያን አሁን ካለችበት ፈተና አውጥተው ወደተሻለ እና አዲስ ምዕራፍ የሚያሻግሩ ጠቃሚ ሀሳቦች መፍለቅ እንደቻሉም ተናግረዋል።
ለዚህም ተመካካሪዎች ላሳዩት ከፍተኛ የሀገር ፍቅር መሥጋና አቅርበዋል።
#Ameco #NationalDialogue #Ethiopia🇪🇹
#ባሕር_ዳር #ነሐሴ_16_2018_ዓ_ም
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
