
በሐረሪ ክልል የሕዝብን ተጠቃሚነት የሚያረጋግጡ የልማት ሥራዎች እየተከናወኑ መኾኑን የክልሉ ምክትል ርእሰ መሥተዳድር ሮዛ ዑመር ገልጸዋል።
ወይዘሮ ሮዛ እና የክልሉ ከፍተኛ መሪዎች በሐረሪ ክልል በከተማ እና በገጠር እየተከናወኑ የሚገኙ የልማት ሥራዎችን ተመልክተዋል።
ምክትል ርእሰ መስተዳድሯ በዚህ ወቅት እንዳሉት በክልሉ በሁሉም አካባቢዎች የሕዝብን ፍትሐዊ ተጠቃሚነት የሚያረጋግጡ የልማት ሥራዎች እየተከናወኑ ነው።
የልማት ሥራዎቹ የሐረሪ ክልልን የማንሠራራት ጅማሮ የሚያመላክቱ እና የሕዝብን ኑሮ የሚቀይሩ ናቸው ብለዋል፡፡
ሕዝብን በማሳተፍ እየተከናወኑ የሚገኙ የልማት ሥራዎችን በፍጥነት እና በጥራት ለማጠናቀቅ በትኩረት እንደሚሠራም አመላክተዋል፡፡
በሂደት ላይ የሚገኙ ነባር ፕሮጀክቶች በሚፈለገው የጥራት ደረጃ እና የጊዜ ሰሌዳ እንዲጠናቀቁ የሚያስችል አቅጣጫ መቀመጡን ጠቅሰዋል።
ከአጠቃላይ የክልሉ በጀት 58 በመቶ የሚኾነው ለኢኮኖሚ ዘርፍ መመደቡን ጠቁመው ይህም የሕዝብን ኑሮ ከማሻሻል ባለፈ ለቀጣዩ ትውልድ ምንዳን ማውረስ ያስችላል ነው ያሉት፡፡
#አሚኮ #ልማት_ሀረሪ #ኢትዮጵያ🇪🇹
#ባሕር_ዳር #ነሐሴ_16_2018_ዓ_ም
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
