“ምንጊዜም በመሣሪያ ያሸነፈ ኃይል የለም” ፕሮፌሰር መስፍን አርዓያ

14

 

በኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን አማካኝነት ባለፉት ሳምንታት ሲካሄድ የቆየው የሀገራዊ ምክክር ጉባኤ የመዝጊያ መርሐ ግብር ዛሬ እየተካሄደ ነው።

በመርሐ ግብሩ ላይ መልዕክት ያስተላለፉት የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ዋና ኮሚሽነር ፕሮፌሰር መስፍን አርዓያ የሀገራዊ ምክክሩ በከፍተኛ ክርክር፣ ውይይት እና በጠንካራ የእርስ በርስ ግንኙነት ሲካሄድ ቆይቷል ብለዋል።

በኢትዮጵያ ታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ በምክክር ሂደት 4 ሺህ ሰዎችን ማሳተፍ እንደተቻለም ገልጸዋል።

ምክክር ይጀመራል እንጂ በማግስቱ አያልቅም ነው ያሉት ዋና ኮሚሽነሩ። ተመካካሪዎች ብዙ ውሳኔዎች ማሳለፋቸውንም አንስተዋል።

“በመሣሪያ ምን ጊዜም ያሸነፈ ኃይል የለም ነው ያሉት። ማሸነፍ የሚቻለው በጋራ ውይይት እንደኾነም ገልጸዋል።

#አሚኮ #ሀገራዊ_ምክክር #ኢትዮጵያ🇪🇹

#ባሕር_ዳር #ነሐሴ_16_2018_ዓ_ም

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!

Previous articleየሻደይ በዓልን ከተቸገሩ ወገኖች ጋር በመረዳዳት ሊከበር እንደሚገባ ብፁዕ አቡነ በርናባስ አሳሰቡ።
Next articleበሐረሪ ክልል የሕዝብን ኑሮ የሚያሻሽሉ የልማት ሥራዎች እየተሠሩ ነው።