የሻደይ በዓልን ከተቸገሩ ወገኖች ጋር በመረዳዳት ሊከበር እንደሚገባ ብፁዕ አቡነ በርናባስ አሳሰቡ።

10

 

የሻደይ በዓል በዋግኽምራ ብሔረሰብ አሥተዳደር በሰቆጣ ደብረ ፀሐይ ወይብላ ቅድስት ማርያም ካቴድራል ሃይማኖታዊ እና ባሕላዊ ሥርዓቱን በጠበቀ መልኩ ተከብሯል።

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያ የዋግኽምራ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ እና የቅዱስ ሲኖዶስ አባል ብጹዕ አቡነ በርናባስ በበዓሉ ላይ ተገኝተው ባስተላለፉት መልዕክት የሻደይ በዓል መሠረቱ የእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ዕርገት መኾኑን አስታውስዋል።

መላዕክት ክንፋቸውን ዘርግተው ቅድስት ድንግል ማርያምን እንዳመሰገኗት ሁሉ ዛሬም ደናግላን የሻደይ ቅጠል አስረው በዓሉን እንደሚያከብሩት ገልጸዋል።

በዓሉ የፍቅር እና የአብሮነት መገለጫ በመኾኑ ኅብረተሰቡ የተቸገሩ ወገኖችን በመደገፍ እና በመረዳዳት ሊያከብረው እንደሚገባ ብፁዕነታቸው አሳስበዋል።

#አሚኮ #የሻደይ_በዓል #ሰቆጣ🇪🇹

#ሰቆጣ #ነሐሴ_16_2018_ዓ_ም

✍️ዘጋቢ፦ ደጀን ታምሩ

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!

Previous articleየበዓላት መድመቂያዎች፤ የአብሮነት መገለጫዎች
Next article“ምንጊዜም በመሣሪያ ያሸነፈ ኃይል የለም” ፕሮፌሰር መስፍን አርዓያ