
ሕገ ወጡ የሕወሃት ቡድን በአማራ ሕዝብ ላይ ያደረሰው ግፍ፣ ጭካኔ እና ሰቆቃ ከውልደቱ ጀምሮ ከ40 ዓመታት በላይ የሚዘልቅ የጥፋት ታሪክ አለው። በማኒፌስቶው በጠላትነት ከመፈረጅ የዘር ማጥፋት ወንጀል እስከመፈጸም የደረሰ በንጹሃን ደም የተነከረ ቡድን ነው።
በሰሜኑ ጦርነት ወቅት ቡድኑ በወረራ በኀይል በያዛቸው አካባቢዎች ሁሉ በሰው ልጅ ላይ ሊፈጸም የማይገመት ግፍ ፈጽሟል። በጭና፣ በማይካድራ እና በቆቦ አጋምሳ ያደረሰው የጅምላ ፍጅት ታሪክ ይቅር የማይለው በአማራ ሕዝብ ላይ ከጣለው የጥቁር ጠባሳ የታሪክ ገጾች መካከል ይጠቀሳሉ።
🚨 በጭና የፈጸመው ዘግናኝ ድርጊት
አካባቢውን በወረረ ወቅት በጭና እና ቦዛ ቀበሌዎች በርካታ ንጹኃን ላይ ለዐይን የሚዘገንን፣ ለጆሮ የሚሰቀጥጥ እና ለመናገር የሚቀፍ ድርጊት ፈጽሟል። ከአንድ ቤት አምሥት የቤተሰብ አባላት በግፍ የተጨፈጨፉበት ድርጊትም ለዚህ አረመኔያዊነት አንዱ ሕያው ማሳያ ነው።
በጥቃቱ ተጎጂ ከነበሩት መካከል አንዲት እናት በወቅቱ ለአሚኮ እንደተናገሩት ሕጻናት ልጆቻቸውን ያለ አሳዳጊ አስቀርተው ቤተሰቦቻቸውን በጭካኔ ገድለውባቸዋል። “ባለቤቴን፣ አባቴን፣ ልጆቼን በግፍ ገደሉብኝ፤ ያለ ሠብሣቢ አስቀሩኝ” በማለት በተሰበረ ስሜትም ይገልጻሉ ተጎጅዋ።
ሕጻናትም “አባታችንን፣ ወንድማችንን፣ አጎታችንን፣ አያታችንን አጥተናል፤ ማንን ይዘን ልንኖር ነው?” እያሉ በልጅ አንደበት ሲያለቅሱ መስማት እጅግ ልብ ይሰብራል፤ ስሜትን ይጎዳል። ሲያለቅሱ ያያቸው ሁሉ አብሮ እንዲያለቅስም ሰብዓዊ ስሜቱ ያስገድደዋል።
ይህ ድርጊት የጥቃት አድራሹን የሕገወጡ ሕወሃት የጭካኔ ጥግ ያሳያል። የቡድኑ የግፍ ጭካኔ እንስሳትን እንኳን ሳይቀር የጨፈጨፈበት አረመኔያዊ ተግባርን ገልጦ አልፏል። የቡድኑን አረመኔያዊ ድርጊት በአግባቡ ለተረዳ ቡድኑ የጨካኝ ሰዎች ሥብሥብ ስለመኾኑ አያጠራጥርም።
🛑የማይካድራ ጭፍጨፋ እና የ7ሺህ ንጹሃን ግድያ
ቹቹ አለባቸው (ዶ.ር) “የተከዜ ፖለቲካ ኃይል፣ ማንነት እና የኢትዮጵያ ብሔራዊ ደኅንነት” በተሰኘው መጽሐፋቸው ላይ እንደገለጹት “ለ40 ዓመታት የሕገወጡ ሕወሃት የጥፋት መርከብ ተጉዞ ተጉዞ ወደቡን ያደረገው ማይካድራ ላይ ነው” በማለት ይገልጹታል።
የሰው ደም የለመደው ሕገወጡ የሕወሃት ቡድን በማይካድራ ከ1ሺህ 560 በላይ ንጹሃንን በግፍ መጨፍጨፉን በመጽሐፋቸው ገልጸውታል።
📌 የአማራ ክልል ዩኒቨርሲቲዎች ፎረም በየካቲት/2015 ዓ.ም ያሳተመው ጥናት እንደሚያመላክተው ቡድኑ በወረራቸው የክልሉ አካባቢዎች ከ7 ሺህ በላይ ንጹኃን ተገድለዋል።
⚠️ ከደም አፍሳሽነት ወደ አዲሱ የቁማር ጥምረት♟️
ዛሬ ላይ የሕገወጡ ሕወሃት ቡድን ይህንን በደል እረስቶ፣ የፈጸመውን ጥቁር ጠባሳ ዘንግቶ፣ በቀደመ የሴራ መንገድ ጉዞውን ቀጥሏል። በዙሪያው ያሉትን ኀይሎች በፖለቲካ ቁማር “የጥምረት” ስም እያሠባሠበ ይገኛል።
በአማራ ሕዝብ ስም ምለው፣ የሕዝብ ጥያቄ እናስመልሳለን ብለው ወደ ጫካ የገቡ ታጣቂዎችም ከሕገወጡ ሕወሃት መሩ የጥፋት ጥምረት ጋር እየሠሩ ስለመኾኑ መሪዎቹ ገልጸዋል።
❓የእነዚያ ሕጻናት እምባ ሳይታበስ፣ ቁስላቸው ሳይሽር፣ በገፍ የተጨፈጨፈው የአማራ ደም ሳይደርቅ፣ እናቶች እርማቸውን ሳያወጡ ዛሬ ከሕገወጡ ሕወሃት ጋር በአንድ መሠለፍ ምን ይባላል? በንጹሃን ደም እንደመቀለድ አይቆጠርምን❓
ሕገወጡ ሕወሃት በቀደመው ጦርነቱ በርካታ የትግራይ ወጣቶችን በማስጨረሱ አሁን ላይ ለዳግም ጦርነት ተቀባይነት ስለማጣቱ የትግራይ ወጣቶች እያጋለጡት ነው።
🎯 ይህንን ክፍተት ለመሸፈን በአማራ ስም የሚንቀሳቀሱ ታጣቂዎችን በእጅ አዙር ለመጠቀም እና “አንተ ሙትልኝ፣ መሬትህን ልውሰድ” የሚል የሴራ እና የቁማር ስልት በጥምረት የዳቦ ስም እየተጠቀመ ስለመኾኑ ልብ ሊባል ይገባል።
#AMECO #StopWar #Ethiopia🇪🇹
#ባሕር_ዳር #ነሐሴ_16_2018_ዓ_ም
✍️በአሰፋ ልጥገበው
ምስል ፦ ከአርካይቭ
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
