
የሻደይ በዓል በሰቆጣ ደብረ ፀሐይ ወይብላ ቅድስት ማርያም ካቴድራል ሃይማኖታዊ ሥርዓቱን ጠብቆ መከበር ጀምሯል።
የቅድስት ድንግል ማርያም ዕርገትን ምክንያት በማድረግ የሚከበረው የሻደይ በዓል በቤተ ክርስትያኗ ሥርዓት መሠረት በዘማርያን ወረብ እና መዝሙር፣ በአባቶች ዝማሜ፣ በሃይማኖቱ ተከታዮች እልልታ ታጅቦ በድምቀት እየተከበረ ይገኛል።
በበዓሉም በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን የዋግ ኽምራ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ እና የቅዱስ ሲኖዶስ አባል ብጹዕ አቡነ በርናባስ፣ የሀገረ ስብከቱ መሪዎች፣ የዋግ ኽምራ ብሔረሰብ አሥተዳደር ከፍተኛ መሪዎች፣ የሰቆጣ ከተማ አሥተዳደር የሥራ ኀላፊዎች፣ ካህናት፣ ዲያቆናት፣ ዘማርያን እና የሃይማኖቱ ተከታዮች ተገኝተዋል።
በከሰዓት መርሐ ግብሩም በአደባባይ እና በመድረክ የሻደይ ተጫዋቾች ባሕላዊ ክዋኔውን ያቀርባሉ ተብሎ ይጠበቃል።
#አሚኮ #ሻደይ #ሰቆጣ 🇪🇹
#ሰቆጣ #ነሐሴ_16_2018_ዓ_ም
በደጀን ታምሩ
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
