
የአሸንድዬ በዓል በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ሃይማኖታዊ መሠረት ያለው በዓል ነው።
አሸንድዬ እና ሶለል በዓላት በሰሜን ወሎ ዞን በድምቀት የሚከበሩ የክረምት በዓላት መኾናቸውን ያነሱት የዞኑ ባሕል፣ ቱሪዝም እና ስፖርት መምሪያ ኀላፊዋ ገነት ሙሉጌታ ናቸው። አሸንድዬ ልጃ ገረዶች በጉጉት የሚጠብቁት በዓል በመኾኑ ዋዜማውን በድምቀት እያከበሩት ነው ብለዋል።
አሸንድዬ የዕኩልነት፣ የአብሮነት እና የመተሳሰብ በዓል በመኾኑ እርቅን እና ፍቅርን ያመጣል ነው ያሉት።
አሸንድዬ ካለው ኢኮኖሚያዊ እና ማኅበራዊ ፋይዳ ባለፈ
ሴቶች የመሪነት ሚናን የሚያሳዩበት በዓል መኾኑንም ገልጸዋል።
በዓሉን በድምቀት ለማክበር ሰፊ ዝግጅት መደረጉን ያነሱት ደግሞ የላሊበላ ከተማ አሥተዳደር ባሕል ቱሪዝም እና ስፖርት ጽሕፈት ቤት ኀላፊ ዲያቆን አዲሴ ደምሴ ናቸው። የአሸንድዬ በዓል በዋዜማው በድምቀት እየተከበረ መኾኑን ተናግረዋል። ልጃ ገረዶች በመሰባሰብ በቤተ ጊዮርጊስ ዋዜማውን በድምቀት ማክበራቸውንም ገልጸዋል።
ከላሊበላ ከተማ አሥተዳደር ኮሙዩኒኬሽን የተገኘው መረጃ እንደሚያመላክተው አሸንድዬ ከባለፉት ዓመታት በተለየ መልኩ በድምቀት እየተከበረ መኾኑን ተናግረዋል።
#አሚኮ #አሸንድዬ #ኢትዮጵያ🇪🇹
#ባሕር_ዳር #ነሐሴ_15_2018_ዓ_ም
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
