
አሚኮ የሻደይን በዓል በዓለም መድረክ እያስተዋወቀ ያለ የባሕል ድምቀት እና መስታወት እንደኾነ የዋግ ኽምራ ብሔረሰብ አሥተዳደር የመንግሥት ኮሙዩኒኬሽን መምሪያ አስታውቋል።
የሻደይ በዓል በሰቆጣ ከተማ ከነሐሴ 16 እስከ 21/16/2018 ዓ.ም ድረስ በተለያዩ ሁነቶች ይከበራል። ይህንን ባሕላዊ ጨዋታ ከነሐሴ ወር መጀመሪያ ጀምሮ አሚኮ የሠራው ዘገባ ሕዝቡን ያነቃ እንደኾነ የተናገሩት የሰቆጣ ከተማ አሥተዳደር የመንግሥት ኮሙዩኒኬሽን ጽሕፈት ቤት ኀላፊ ሰሎሞን መዓዛ ናቸው።
ሻደይ ለዋግ ሕዝብ ታሪኩ እና ማንነቱ ነው ያሉት ኀላፊው ይህንን የዋግ መገለጫ በዓል አሚኮ የሰጠው ትኩረት የሚመሰገን ነው ብለዋል።
ለባሕል እድገት አሚኮ በትጋት የሚሠራ መኾኑን የገለጹት ደግሞ የጻግቭጅ ወረዳ የመንግሥት ኮሙዩኒኬሽን ጽሕፈት ቤት ኀላፊ ጌታወይ ሹሜ ናቸው። ይህም በሕዝቡ ዘንድ ያለውን ተቀባይነት ከማጉላቱ ባሻገር የሕዝብ ለሕዝብ አንድነትን ፈጥሯል ብለዋል።
ሻደይን የዋግ ኽምራ ልጃገረዶች ከ2 ሺህ ዓመታት በፊት ለዓለም ሕዝቦች ያበረከቱት የነጻነት እና የሴቶችን እኩልነት ያረጋገጠ በዓል መኾኑን የተናገሩት ደግሞ የብሔረሰብ አሥተዳደሩ የመንግሥት ኮሙዩኒኬሽን መምሪያ ኀላፊ ከፍያለው ደባሽ ናቸው።
ይህንን እውነታ ለዓለም ለማሳየት ደግሞ አሚኮ ከፊት መሰለፉ የሚደነቅ ነው ብለዋል። አሁንም የሻደይ በዓል ተጀምሮ እስኪጠናቀቅ ድረስ ከዋግ ሕዝብ ጎን በመቆም ለሻደይ ባሕላዊ የልጃገረዶች ጨዋታ ለዓለም ሕዝብ ማሳየቱን እንዲቀጥልም ጠይቀዋል።
ዘጋቢ፦ ደጀን ታምሩ
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
