
የሐረሪ ክልል ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት የክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎት እና ኢኒሼቲቮችን ገምግሟል።
የክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎት የብልጽግና ፓርቲ ሰው ተኮር እሳቤ ተግባራዊ መገለጫ መኾኑን የተናገሩት የሐረሪ ክልል ብልጽግና ፓርቲ ጽሕፈት ቤት ኀላፊ ጌቱ ወዬሳ ናቸው።
በክረምት በጎ ፈቃድ ተግባራት ዜጎችን ተጠቃሚ በማድረግ አበረታች ውጤቶች እየተመዘገበ እንደኾነም አንስተዋል።
የኅብረተሰቡን ችግር የሚፈቱ እና ተጠቃሚነትን የሚያረጋግጡ ተግባራት ላይ ትኩረት ተሰጥቶ እየተሠራ እንደሚገኝም ገልጸዋል።
በዚህም የአረጋውያን እና አቅመ ደካሞችን መኖሪያ ቤት እድሳት እና መልሶ ግንባታ፣ የአካባቢ ንጽሕ እና ጥበቃ፣ የችግኝ ተከላ፣ የደም ልገሳ፣ የማጠናከሪያ ትምህርት መስጠት እና የትምህርት ቁሳ ቁስ ድጋፍ የማሠባሠብ ሥራዎች ተጠናክረው መቀጠላቸውን ገልጸዋል።
የክረምት በጎ ፈቃድ ተግባራት የብልጽግና ፓርቲ ሰው ተኮር እሳቤ ማሳያ ነው ያሉት ኀላፊው የማኅበረሰቡን ተጠቃሚነት የሚያረጋግጡ ተግባራት ተጠናክረው ይቀጥላሉ ብለዋል።
በክልሉ አምራች እና ሸማቹን በቀጥታ በማገናኘት የኑሮ ውድነትን ለማረጋጋት የተጀመሩ የቅዳሜ ገበያዎች ተጠናክረው ሊቀጥሉ እንደሚገባም ገልጸዋል።
መሪዎች ለፋይዳ ብሔራዊ መታወቂያ እና የ7 ሚሊዮን ኮደርስ ሥልጠና ልዩ ትኩረት በመስጠት እንዲሠራ አቅጣጫ አስቀምጠዋል።
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
