
የውበት ሰገነቷ ባሕር ዳር ከተማ ከተፈጥሮ ውበቷ እና ከታሪክ ሃብቷ ጋር ጸጋ ተደራርቦ የተሰጣት ከተማዋ በኮሪደር ልማት አምራ፣ ደምቃ፣ ተሞሽራ እና ጣናን ተንተርሳ ኑ ይጎብኙን እያለች ትገኛለች።
ባሕር ዳር ከተማ ስትታሰብ የጣና ሐይቅ፣ የባሕር ዳር ዓሣ እና ሌሎችም በረከቶች በውስጧ አብረው ይነሳሉ።
ከጣና የሚመጣው ለስላሳ የአየር ጸባይ የከተማዋ ለየት ያለ መልክ እና ጸጋ ነው። ይህም ከቱሪዝም የሚገኘውን ኢኮኖሚ በእጅጉ እያነቃቃ እና እያሳደገ ይገኛል።
ከተማዋ የቱሪዝም መዳረሻነቷ ከጊዜ ወደ ጊዜ ይበልጥ እየጎላ የመጣችው ውቢቷ ባሕር ዳር ከተማ የቱሪዝም ዘርፉን ይበልጥ የሚያቀላጥፍ እና ዓለም አቀፍ ተደራሽነቷን የሚያሰፋ ታላቅ ምዕራፍ ላይ ትገኛለች።
ባሕር ዳር ከተማ በርካታ የተፈጥሮ እና ሰው ሠራሽ የቱሪዝም ሀብቶች ያሏት ከተማ ናት። የጣና ሐይቅ ገዳማት፤ ደሴቶች፣ የኮሪደር ልማት እና የተለያዩ መዝናኛ ሥፍራዎች ተፈጥሯዊ ውበታቸውን ጠብቀው የሚገኙ እና የብዙዎችን ቀልብ የሚስቡ ስፍራዎች ናቸው።
በከተማዋ የሚገኙ ደረጃቸውን የጠበቁ ሆቴሎች፣ የውኃ፣ የየብስ እና የአየር ትራንስፖርት አማራጮች ለቱሪስቶች የጉዞ ቆይታ ልዩ ውበት ሰጥተዋቸዋል።
በከተማዋ የተለያዩ የዕደ ጥበብ ውጤቶች እና ሌሎችም ለዕይታ ማራኪ ገጽታዎች አላቸው። ይህም ጎብኝዎች በከተማው ውስጥ የሚቆዩበትን ጊዜ እንዲያራዝሙ ትልቅ ዕድል ይሠጣል ።
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
