በሐረሪ ክልል 231 ኢንዱስትሪዎች ወደ ሥራ ገብተዋል።

8

 

በሐረሪ ክልል በመደመር እሳቤ በተተገበሩ የኢንዱስትሪ ልማት ሥራዎች 231 አነስተኛ፣ መካከለኛ እና ከፍተኛ ኢንዱስትሪዎች ወደ ሥራ በመግባት በዘርፉ ከፍተኛ እመርታ መመዝገቡ ተገልጿል።

የብዝኀ ዘርፍ ኢኮኖሚ መርህን የሚከተለው የመደመር መንግሥት የኢትዮጵያን ሁለንተናዊ ብልጽግና ለማረጋገጥ ትኩረት ከሰጣቸው ስትራቴጂያዊ የኢኮኖሚ አምዶች አንዱ የኢንዱስትሪ ልማት ነው።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር) “የመደመር መንግሥት” በተሰኘው መጽሐፋቸው ላይ እንዳመላከቱት ዘርፉ ከባሕላዊ እና ከተበታተነ አሠራር ወጥቶ በቴክኖሎጂ እና በፈጠራ በፍጥነት ወደ ላቀ ምርታማነት እንዲሸጋገር በርካታ መዋቅራዊ ሪፎርሞች እና ሀገራዊ ንቅናቄዎች ተተግብረዋል።

ከሀገራዊ ለውጡ ማግስት ጀምሮ በሐረሪ ክልል ለኢንዱስትሪው ዘርፍ በተደረገው ልዩ ድጋፍ እና ክትትል አምራች ኢንዱስትሪዎች ከኀይል አቅርቦት እና ከመሠረተ ልማት ጋር በተያያዘ ይገጥሟቸው የነበሩ ማነቆዎች በመፈታታቸው በርካታ ተቋማት ወደ ሙሉ የማምረት እንቅስቃሴ መሸጋገር ችለዋል።

በተጨማሪም የማምረት አቅምን ለማነቃቃት የተጀመረው “የኢትዮጵያ ታምርት” ንቅናቄ የኢንዱስትሪዎችን ምርታማነት በማሳደግ ከውጭ የሚገቡ ምርቶችን በሀገር ውስጥ ለመተካት እና ወደ ውጭ በሚላኩ ምርቶች ላይ እሴት በመጨመር የውጭ ምንዛሪ ግኝትን ለማሳደግ ከፍተኛ አስተዋጽኦ ማበርከቱ ተጠቁሟል።

የዘርፉ ማደግ ለበርካታ ዜጎች የሥራ ዕድል ለመፍጠርም አስችሏል።

በቀጣይም በክልሉ አዳዲስ ኢንቨስትመንቶችን በመሳብ በተለይም በኮንስትራክሽን፣ በምግብ እና መጠጥ፣ በቆዳ እና የቆዳ ውጤቶች እንዲሁም ሌሎች ዘርፎች ላይ የማስፋፋት እና የማዘመን ተግባራት ተጠናክረው እንደሚቀጥሉም ታውቋል።

#Ameco #HarariRegion #EthiopiaTamrt #IndustrialDevelopment

#ባሕር_ዳር #ነሐሴ_11_2018_ዓ_ም

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!

Previous articleበምግብ ዋስትና እና ልማታዊ ሴፍቲኔት ሥራ ፕሮጀክት የትምህርት ተቋማት እየተገነቡ ነው።
Next articleሀገራዊ የምክክር ሂደቱን ገለልተኝነት፣ አካታችነትና ተሳትፎ በተመለከተ ከኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን የተሰጠ መግለጫ