8
በአዲስ አበባ የከተማ ነዋሪው ቁጥር እየጨመረ ከመምጣቱ እና የከተማው ልማት እያደገ ከመምጣቱ ጋር ተያይዞ የንጹሕ መጠጥ ውኃ ፍላጎት እየጨመረ መጥቷል። በተመሳሳይ የሚወገድ ፈሳሽ ቆሻሻም መጠኑ እያደገ ነው።
በዚህም በተያዘው በጀት ዓመት የአዲስ አበባ ከተማ አሥተዳደር የውኃ እና ፍሳሽ ባለሥልጣን በንጹሕ መጠጥ ውኃ አቅርቦት እና በፍሳሽ ቆሻሻ አወጋገድ መስክ በርካታ ተግባራትን አከናውኗል። ባለሥልጣኑ ገንብቶ ያጠናቀቃቸውን የንጹሕ መጠጥ ውኃ እና የፍሳሽ ቆሻሻ ማስወገጃ ተቋማትን ወደ ሥራ አስገብቷል።
የአዲስ አበባ ከተማ አሥተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ በከተማው ያለውን የንጹሕ መጠጥ ውኃ ፈላጎት ለማሟላት እና ፍሳሽ ቆሻሻን ለማስወገድ በርካታ ተግባራት መከናወናቸውን ገልጸዋል።
የአዲስ አበባ ከተማ ውኃ እና ፍሳሽ ባለሥልጣን ሥራ አሥኪያጅ ኢንጅነር ዘሪሁን አባተ በተያዘው በጀት ዓመት ጥልቅ የንጹሕ ውኃ ጉድጓድ ቁፋሮ እና የፍሳሽ ቆሻሻ ማስወገጃ ግንባታ መሠራቱን አንስተዋል። በ2018 በጀት ዓመት ብዛታቸው 20 ጥልቅ የውኃ ጉድጓዶች ተቆፍረው ለአዲስ አበባ ከተማ ንጹሕ ውኃ እንድቀርብ ተደርጓል ብለዋል።
የከተማውን የፍሳሽ ቆሻሻ አያያዝ ለማሻሻል ከሚሠሩ ተግባራት መካከል የፍሳሽ ቆሻሻ ማስወገጃ ግንባታ አንዱ ሲኾን ኮዬ የፍሳሽ ማጣሪያ በቀን 20 ሺህ ኪዩቢክ ሜትር ፍሳሽ ቆሻሻን ለማጣራት ያስችላል ነው ያሉት። ይህም የከተማውን ፍሳሽ ቆሻሻ የማጣራት አቅም ወደ 253 ሺህ ኪዩቢክ ሜትር ያሳድገዋል ብለዋል።
የንጹሕ መጠጥ ውኃ አቅርቦቱን ለማሻሻል እና የፍሳሽ ቆሻሻን ማስወገጃ ለመገንባት ለሚከናወነው ተግባር አስተዋጽኦ ላደረጉ አካላት ከንቲባ አዳነች አቤቤ ምስጋና አቅርበዋል።
ዘጋቢ፦ ተመስገን ዳረጎት
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
Previous articleየባሩድ ጭስ ሳይኾን የብዕር ማዕዛን ለተማሪዎች መፍቀድ ግድ ይላል!
Next articleየባሩድ ጭስ ሳይኾን የብዕር ማዕዛን ለተማሪዎች መፍቀድ ግድ ይላል!