
በከተማዋ እየተሠራ የሚገኘው የኮሪደር ልማት የቱሪዝም ፍሰቱን ለማሳደግ ሚናው የጎላ መኾኑን የደባርቅ ከተማ ነዋሪዎች ገልጸዋል።
ደባርቅ ከተማ በሰሜን ተራራዎች ብሔራዊ ፓርክ በቅርብ ርቀት የምትገኝ የተሻለ የቱሪዝም ፍሰት ካላቸው ከተሞች መካከል አንዷ ናት።
የደባርቅ ከተማ አሥተዳደር ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ ጌትነት ጸጋዬ ደረጃውን የጠበቀ የመሠረተ ልማት ሥራዎችን በማከናወን ምቹ እና ለነዋሪዎች ተስማሚ አካባቢን ለመፍጠር እየተሠራ ነው ብለዋል።
የኮሪደር ልማቱ ከአካባቢው ማኅበረሰብ በተጨማሪ ወደ ስፍራው ለሚመጡ ጎብኝዎች ምቹ ሁኔታ መፍጠር በሚያስችል መልኩ እየተከናወነ እንደሚገኝም ነው የተናገሩት።
ሀሳባቸውን የሰጡ የከተማዋ ነዋሪዎች እየተሠራ የሚገኘው የኮሪደር ልማት የቱሪዝም ፍሰቱን ለማነቃቃት እንደሚያግዝ ገልጸዋል።
የኮሪደር ልማቱ በተሳካ ሁኔታ ተጠናቅቆ አገልግሎት እንዲሰጥ ለማስቻልም ድጋፋቸውን አጠናክረው እንደሚቀጥሉ አንስተዋል።
የደባርቅ ከተማ አሥተዳደር በከተማዋ የተጀመረውን የኮሪደር ልማት ይበልጥ ለማጠናከር በአዲስ አበባ እና በሌሎች ከተሞች የገቢ ማሰባሰቢያ መርሐ ግብር ለማካሄድ እየሠራ ይገኛል።
#አሚኮ #ቱሪዝም #ኢትዮጵያ🇪🇹
#ባሕር_ዳር #ነሐሴ_09_2018ዓ_ም
በደረጀ ደርበው
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
