በደብረታቦር ቀጣና የተሠማራው የምሥራቅ ዕዝ ኮር የፅንፈኞችን የጥፋት መሰናክሎች በማፅዳት ሰላም እያሰፈነ ነው።

18

 

የምሥራቅ ዕዝ ኮር ከደብረታቦር ከተማ አሥተዳደር አመራሮች፣ ከፀጥታ አካላት እና ከተለያዩ ባለድርሻ አካላት ጋር በወቅታዊ የሰላም ጉዳዮች ዙሪያ ውይይት አድርገዋል።

የኮሩ አዛዥ ኮሎኔል ሰጥየ አራጌ በውይይቱ ላይ እንደገለጹ ኮሩ በቀጣናው ከተሰማራበት ጊዜ ጀምሮ የፅንፈኞችን የጥፋት መሰናክሎችን በማፅዳት በአከባቢው ሰላምና መረጋጋት እንዲመጣ ውጤታማ ሥራ ተሠርቷል። ለተገኘው አንጻራዊ ሰላም የአከባቢው ማኅበረሰብ እና የዞኑ ጥምር የፀጥታ ኃይሎች ከባለ ድርሻ አካላት ጋር ከሠራዊቱ ጎን በመሆን አስተዋጽኦ ማድረጋቸውን ገልጸዋል። የከተማውን ሰላምና ደህንነት አጠንክረው እንዲያስቀጥሉም አስገንዝበዋል።

የደብረ ታቦር ከተማ ከንቲባ ደሴ መኮንን የከተማዋን ሰላምና ፀጥታ ለማስጠበቅ የሠራዊቱ ሚና ከፍተኛ መሆኑን ጠቅሰዋል። የከተማው አመራርና የፀጥታ አካላቱም ከመከላከያ ሠራዊቱ በገባበት ቦታ ሁሉ በመግባት የከተማው እና የማኅበረሰቡን ደህንነት ለመጠበቅ ሁልጊዜም ዝግጁ መሆናቸውን ተናግረዋል።

አሁንም ቢኾን የሚላላኩ የጠላት ሴሎችን ከከተማውና ከማኅበረሰቡ ነጥለው ለማውጣት እና ለሕዝቡ ምቹ የሰላም መንገድ ለመፈጠር የበኩላችንን ድርሻ እንደሚወጡም የከተማ አሥተዳደሩ የጸጥታ አካላት ገልጸዋል።

ዘገባው የምሥራቅ ዕዝ ነው።

#አሚኮ #Defencenews #Ethiopia🇪🇹

Previous articleሀገራዊ ምክክሩ አሁን ምን ደረጃ ላይ ነው?
Next articleበጋራ ቁርጠኝነት ትምህርት ቤቶችን መክፈት፣ መልሶ መገንባት እና ተስፋን መዝራት ያስፈልጋል።