ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር) ያስተላለፉት መልእክት፦

3

ኢትዮጵያን ከወጣቶቿ ነጥሎ ማየት አይቻልም!

የሕዝባችን የእድሜ ስብጥር እንደሚያመላክተው ወጣቶች ከፍተኛውን ቁጥር መያዛቸው፣ ብልጽግናን ለማረጋገጥና ለማፅናትም ታላቅ እድል ነው።

‎የኢትዮጵያ ወጣት መልካም ዓላማን አንግቦ የሚንቀሳቀስ፣ የለውጥ ዋነኛ ሞተርና የሉዓላዊነታችን ጽኑ ማገር ነው! የኢትዮጵያ ወጣት የሀገሩን ታሪክ በአዲስ ብዕርና ብራና እየጻፈ ይገኛል። ሀገራችንን የኋሊት ጠፍንገው የያዟትን አጓጉል ልማዶች፣ አላስፈላጊ ንትርኮች፣ ጭቅጭቅ እና ግጭቶች በመራቅ የአሁን ወጣት በልማት ላይ አተኩሯል፣ ድህነትን ተጠይፏል።

የመደመር መንግሥት የወጣቶችን ሁለንተናዊ ተጠቃሚነትና የአመራርነት ሚና ለማጠናከር በትኩረትና በቁርጠኝነት እየሰራ ይገኛል።

‎ሀገራዊ ርዕያችንን ዕውን ለማድረግ ሁላችሁም በንቃት እየተጋን፣ በፍቅር እንድንመላለስ ጥሪዬን አቀርባለሁ።

#አሚኮ #የወጣቶች_ቀን #ኢትዮጵያ

Previous articleአፈር እና ውኃን ያስታረቀው የወጣት ጋሻው ተሞክሮ