ሀገራዊ ምክክር፤ ለኢትዮጵያውያን አዲስ ፍኖት

10

🇪🇹ሀገራዊ ምክክር፤ ለኢትዮጵያውያን አዲስ ፍኖት 🌅

​በኢትዮጵያ ሀገራዊ መግባባትን ለመፍጠር ያለመ የምክክር ጉባኤ በታላቅ ተስፋ እየተካሄደ ይገኛል።ጉባኤው ባለፉት ዓመታት የተከሰቱ ግጭቶችን እና የሀሳብ ልዩነቶችን በውይይት በመፍታት ኢትዮጵያን ወደ ተሻለ ምዕራፍ እንደሚያሸጋግር የታመነበት ነው።💡🔄

​በዚህ ታሪካዊ ሁነት ላይ እየተሳተፉ የሚገኙት ልዩ ልዩ የኅብረተሰብ ተወካዮች በሂደቱ ዙሪያ አስተያየታቸውን ሰጥተዋል።

የምክክሩ ተሳታፊ ​ወይዘሮ ነጻነት ሲሳይ እንደተናገሩት ሀገራዊ ምክክሩ ሁሉንም የማኅበረሰብ ክፍል ያካተተ እጅግ አሳታፊ መኾኑን ገልጸዋል። ችግሮችን እና የሀሳብ ልዩነቶችን በአጀንዳነት ሠብሥቦ በመወያየት መፍትሔ ለማምጣት ምክክሩ ትልቅ አጋጣሚ መኾኑን ተናግረዋል።🕊️

ሌሎቹ ተሳታፊዎች አቶ ዲናሞ ኡሞጎ እና አቶ ደረጀ ቦጋለ በሰጡት አስተያየትጉባኤው ከዳር እስከ ዳር ያሉ ኢትዮጵያውያንን ያሠባሠበ እና ከሁሉም ክልሎች የመጡ ልዩ ልዩ ሀሳቦች የሚንጸባረቁበት ጉባኤ መኾኑን ተናግረዋል።

ዜጎች ሀገራቸውን የሚያሻግር ሀሳብ በጋራ እያዋጡ እና
የምክክር ሂደቱ በጥሩ ሁኔታ እየተከናወነ እንደሚገኝ የውይይቱ ተሳታፊዎች አስተያየታቸውን ሰጥተዋል።

በምክክሩ የማይጠቅሙ ትርክቶችን በመተው አዲስ መሠረት በመጣል ኢትዮጵያን የተሻለ ደረጃ ላይ ለማድረስ መፍትሄ እንደሚያመጣ አስተያየታቸውን ሰጥተዋል። በምክክር ሂደቱ እያንዳንዱ ተሳታፊ የሚሰማውን ስሜት እና ሀሳብ በሙሉ ነጻነት እየገለጸ እንደሚገኝ አረጋግጠዋል።

የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ዋና ኮሚሽነር ፕሮፌሰር መስፍን አርዓያ እንደገለጹት ሂደቱ በተለያዩ ቡድኖች ሀሳቦች እየተንሸራሸሩ፣ መተማመን እየተፈጠረ፣ ቃለጉባኤ እየተያዘ እና እየተሰነደ በጥሩ ሁኔታ እየሄደ እንደሚገኝም ጠቁመዋል።

ሀገራዊ ምክክሩ ኢትዮጵያውያን በነጻነት ተወያይተው የጋራ ርዕይ እንዲቀርጹ እና ካለፉት ችግሮች ተሻግረው አዲስ የታሪክ ምዕራፍ እንዲከፍቱ ትልቅ መንገድ የሚከፍት ነው።

#Ameco #Nationaldialogue #Ethiopia 🇪🇹

#ባሕር_ዳር #ነሐሴ_04_2018_ዓ_ም

ዘጋቢ:- አሰፋ ልጥገበው

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!

Previous article“ወደ ጫካ የወጣነው ምክክር ባለመኖሩ ነው” ካፒቴን ማስረሻ ሰጤ