
በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል በአንድ ጀምበር 800 ሚሊዮን ችግኞችን የመትከል መርሐ ግብር እየተካሄደ ይገኛል።
በክልሉ በሁሉም አከባቢዎች በተጀመረው በዚህ መርሐ ግብር የተለያዩ የኅብረተሰብ ክፍሎች በነቂስ ወጥተው በችግኝ ተከላ እየተሳተፉ ነው።
የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ጥላሁን ከበደ በመርሐ ግብሩ ችግኝ በተከሉበት ወቅት፣ ዛሬ ተስፋ ተክለን ልጆቻችን የበለፀገች ኢትዮጵያ እናስወርሳለን ብለዋል።
ችግኝ የመትከል እና የመንከባከብ ጉዳይ ባህል ሊደረግ እንደሚገባ ገልጸው፣ በክልሉ የመሬት ናዳን የመሳሰሉ የተፈጥሮ አደጋዎች በየጊዜው እንደሚፈጠሩና ይህንን ለመከላከል ሁላችንም ችግኞችን እንትከል አካባቢያችን እንጠብቅ ነው ያሉት።
