የእንጅባራ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ በተለያዩ የትምህርት መስኮች ያሠለጠናቸውን ተማሪዎች አስመረቀ።

10
ኮሌጁ በ10 የትምህርት መስኮች በደረጃ 4 እና በደረጃ 5 ያሠለጠናቸውን ተማሪዎች ነው ያስመረቀው።
የእንጅባራ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ዲን እምቢያለ መርከቡ ኮሌጁ ከተቋቋመበት ከ1994 ዓ.ም ጀምሮ እስከ አሁን ድረስ ከ10 ሺህ በላይ ተማሪዎችን አሠልጥኖ በማስመረቅ እና ብቁ የሰው ኃይል በማፍረት ሂደት ገንቢ ሚና መጫወቱን ተናግረዋል።
የዕለቱ ተመራቂዎችም ለደረጃቸው የሚመጥነውን የጽንሰ ሀሳብ እና የተግባር ሥልጠና በአግባቡ ተከታትለው ያጠናቀቁና ብቁ መኾናቸውን ገልጸዋል።
ኮሌጁ ከሚሰጠው ሥልጠና ባሻገር አዳዲስ ችግር ፍቺ ቴክኖሎጂዎችን በማፍለቅ ለአካባቢው ማኅበረሰብ እያቀረበ መኾኑንም ተናግረዋል።
ኮሌጁ የትምህርት ሥራ አመራር ሥርዓትን ተግባራዊ በማድረግ በሥልጠና፣ በቴክኖሎጂ ሽግግር እና በኢንዱስትሪ ኤክስቴንሽን አገልግሎት ድጋፍ ከዓለም አቀፍ መስፍርቶች አንጻር ተስማሚነቱ ተረጋግጦ የእውቅና ሰርትፊኬት ማግኘቱንም አንስተዋል።
በመርሐ ግብሩ ላይ የተገኙት የእንጅባራ ከተማ አሥተዳደር ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ እና የኮሌጁ ሥራ አመራር ቦርድ ሰብሳቢ የኔዓለም ዋሴ ኮሌጁ በቴክኖሎጂ የተደገፈ ጥራት ያለው ሥልጠና በመስጠት ለአካባቢው ልማት ገንቢ ሚና እየተጫወተ መኾኑን ተናግረዋል።
ምሩቃን በሥልጠና ወቅት ያገኙትን ዕውቀት እና ልምድ በመጠቀም ቀጣይ እራሳቸውን ለማሻሻል መትጋት እንዳለባቸውም አስገንዝበዋል።
ተመራቂ ተማሪዎችም በኮሌጅ ቆይታቸው ያገኙትን እውቀት እና ልምድ በመጠቀም ሥራ ፈጥረው ለመሥራት ዝግጁ መኾናቸውን አረጋግጠዋል።
በዕለቱ በኮሌጅ ቆይታቸው የላቀ ውጤት ላስመዘገቡ ተማሪዎች የዋንጫ እና የሜዳሊያ ሽልማት ተበርክቶላቸዋል።
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
Previous articleበቀብሪበያህ ወረዳ በደረሰ የትራፊክ አደጋ የ12 ሰዎች ሕይዎት አለፈ።
Next articleየእኛ እናውቅላችኋለን የፖለቲካ አካሄድ ጊዜው አብቅቷል