
በሶማሌ ክልል ቀብሪበያህ ወረዳ በደረሰ የመኪና አደጋ የ12 ሰዎች ሕይወት አልፏል።
የሶማሌ ክልል ርእሰ መሥተዳድር ሙስጠፋ ሙሐመድ በቀብሪበያህ ወረዳ በደረሰ የትራፊክ አደጋ ሕይዎታቸውን ባጡ ወገኖች የተሰማቸውን ሀዘን ገልጸዋል።
አደጋው ዛሬ ንጋት ላይ በቀበሪበያህ ወረዳ ጉዮው ቀበሌ በባለ ሦስት እግር ተሽከርካሪ እና በአይሱዙ ጭነት ተሽከርካሪ መካከል በደረሰ ግጭት በ12 ሰዎች ላይ የሞት እና በ3 ሰዎች ላይ ደግሞ የመቁሰል አደጋ የደረሰ ሲኾን የአደጋው መንስኤ በፖሊስ እየተጣራ እንደሚገኝ ከሶማሌ ክልል የመንግሥት ኮሙዩኒኬሽን የተገኘው መረጃ ያመለክታል።
አሚኮ በመኪና አደጋው ምክንያት ሕይዎታቸው ላለፈባቸው ቤተሰቦች መጽናናትን ይመኛል።
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
