
የወይዘሮ ስኂን ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ በደረጃ 4 እና 5 በመደበኛ እና በማታ መረሐ ግብር ያሠለጠናቸውን ከ400 በላይ ሠልጣኞች አስመርቋል።
ተመራቂ ሠልጣኞች በሠለጠኑበት ሙያ ሀገራቸውን እና ወገናቸውን ለማገልገል መዘጋጀታቸውን ተናግረዋል።
በተመረቅንበት ወቅት ኢትዮጵያ መምከሯ የቀጣዩን ገዞ የተሳካ ያደርገዋል ያሉት ተመራቂዎቹ ለሀገራዊ ምክክሩ ስኬታማነት ሁሉም የድርሻውን መወጣት እንዳለበትም ጠይቀዋል። ኢትዮጵያ እየመከረች ባለችበት ወቅት መመረቃችን ተስፋችንን ያለመልመዋል ብለዋል።
የወይዘሮ ስኂን ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ዲን ሰለሞን ይመር ተመራቂዎች በንድፈ ሀሳብ እና በተግባር ያገኙትን ዕውቀት ተጠቅመው ለሀገራቸው የመፍትሔ አካል መኾን እንደሚገባቸው ገልጸዋል። የቤተሰብ፣ የመምህራን እና የሠልጣኞች ጥረት ተደምሮ ለምረቃ በቅታችኃል ያሉት ዲኑ ሥራ ፈጣሪ በመኾን ለሌሎች ወጣቶች ተምሳሌት መኾን እንዳለባቸውም አስገንዝበዋል።
የደሴ ከተማ አሥተዳደር ምክትል ከንቲባ ሽመልስ ጌታቸው ወቅቱ የሚጠይቀውን ዲጂታላይዝድ እና ሙያ ተኮር ሥልጠና መውሰዳችሁ የሚሰጣችሁን ኀላፊነት በአግበቡ ለመወጣት ያግዛል ብልዋል።
ዘመኑ የፈጠረውን ቴክኖሎጅ በመጠቀም ማኅበረሰባዊ ችግሮችን ለመፍታት ሠልጣኞች በየጊዜው ብቃታቸውን እና ክህሎታቸውን እንድያሳድጉ አሳስበዋል።
#አሚኮ_ዜና #የወይዘሮስኂንፖሊቴክኒክኮሌጅ #ምረቃ
#ደሴ #ሐምሌ_11_2018ዓ_ም
ዘጋቢ፦ ባለ ዓለምየ
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
