
የቀድሞው የትግራይ ክልል ርእሰ መሥተዳድር ገብሩ አስራት ሕገወጡ የሕወሃት የጥፋት ቡድን ከአምባገነንነት ወደ አሸባሪነት ሙሉ በሙሉ መሸጋገሩን ገልጸዋል።
አቶ ገብሩ አስራት በትግራይ ወቅታዊ ሁኔታ ላይ በሰጡት አሳሳቢ አስተያየት፣ ሕገ-ወጡ የሕወሃት ቡድን ለጠበበ ቡድናዊ ጥቅሙ እና ሥልጣኑ ሲል ብቻ የትግራይ ሕዝብ ታሪካዊ ጠላት ከኾነው የሻዕቢያ ቡድን ጋር መጣመሩን ይፋ አድርገዋል። ቡድኑ የትግራይ ወጣቶችን እያፈሰ ለገበያ እና ለሽያጭ እያቀረበ እንደሚገኝም በምሬት ተናግረዋል።
🛑 አቶ ገብሩ አስራት እንዳሉት ሻዕቢያ የትግራይ ሕዝብ ብቻ ሳይሆን የመላው ኢትዮጵያ ጠላት መኾኑን ገልጸዋል።
በፕሪቶሪያው የሰላም ስምምነት ሻዕቢያ መበሳጨቱን የጠቀሱት አቶ ገብሩ ስምምነቱ ከተፈረመ በኋላ ስምምነቱን እንዳልወደደው በሚዲያዎቹ በይፋ መግለጹን አስታውሰዋል።
ትግራይን ዳግም የጦርነት እና የደም ማዕከል ለማድረግ ‘ፅምዶ’ በሚል ስያሜ ከሕገ ወጡ የሕወሃት ቡድን ጋር የተጣመረው ፀረ ኢትዮጵያዊው የሻዕቢያ ኀይል የትግራይን ሕዝብ ከምድረ ገጽ ለማጥፋት ከቅጥረኞቹ ጋር እየሠራ እንደሚገኝ አብራርተዋል።
የቀድሞው ርእሰ መሥተዳድር አክለውም በአሁኑ ወቅት ይሄው ሕገ ወጡ የሕወሓት የጥፋት ቡድን የትግራይ ወጣቶችን እያፈነ ለዳግም ጦርነት በገንዘብ እየሸጣቸው እንደሚገኝ እና ይሄም በወጣቱ ላይ እየተፈጸመ ያለ ትልቅ ክህደት እና ዘር ማጥፋት መኾኑን በቁጭት ገልጸዋል።
#AMICO #ትግራይ #ኢትዮጵያ #ወቅታዊሁኔታ
#አዲስ_አበባ፡ሐምሌ11/2018 ዓ.ም
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
