“በሐረሪ ክልል የአውሮፕላን ማረፊያ ግንባታ ፕሮጀክት በራስ አቅም ለመገንባት ይሠራል” ርዕሰ መሥተዳድር ኦርዲን በድሪ

6

 

በሀረሪ ክልል በ2019 በጀት ዓመት የክልሉን ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ እድገት በላቀ ደረጃ ለማሻሻል እንደሚሠራ የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ኦርዲን በድሪ ገልጸዋል።

የክልሉን ሁለገብ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥም የአውሮፕላን ማረፊያ ግንባታ ፕሮጀክት በራስ አቅም፣ በሕዝብና በመንግሥት አጋርነት ለመገንባት በ2019 በጀት ዓመት የዝግጅት ምዕራፍ ሥራዎች በይፋ ይጀመራሉ ብለዋል።

ርዕሰ መስተዳድሩ “ይህ ሥራ ከፍተኛ ጥረትና ተነሳሽነትን የሚጠይቅ ፈታኝ ፕሮጀክት ቢሆንም፤ ልክ እንደ ኮሪደር ልማት ሥራችን ሁሉ ለወደፊት ትውልድ የሚተላለፍ የላቀ የጋራ አሻራ ሆኖ የሚቀጥል ነው” ብለዋል።

​የአውሮፕላን ማረፊያ ግንባታው የክልሉን የንግድ እንቅስቃሴ፣ የቱሪዝም ፍስሰት እና የኢንቨስትመንት አማራጮችን በማሳደግ የሕዝቡን የኑሮ ሁኔታ በዘላቂነት ለመቀየር ቁልፍ ሚና እንደሚጫወትም ገልጸዋል።

​የክልሉ መንግሥት ፕሮጀክቱን በተያዘለት ጊዜና ጥራት ለማጠናቀቅ ከኅብረተሰቡ ጋር በቅርበት እንደሚሠራ የገለጹት ርዕሰ መስተዳድሩ፣ መላው የክልሉ ሕዝብ ለዚህ ታላቅ የልማት ሥራ ስኬታማነት አስፈላጊውን ድጋፍና ትብብር እንዲያደርግም ጥሪ አቅርበዋል።

#አሚኮ #ሐረር #ኢትዮጵያ

#ሐምሌ_10_2018_ዓ_ም

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!

Previous article‘ሁሉም የተሳተፉበት፣ ያለ ልዩነት የተካተቱበት‌”
Next article🧵🤝🏾 የገናናዋ ኢትዮጵያ ንጋት ማብሰሪያ🌅🇪🇹