የሀገራዊ ምክክር ጉባኤው ዋና ዋና ከዋኞች እነማን ናቸው?🤝

9

 

የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን እያስተባበረ በሚገኘው የሀገራዊ ምክክር ጉባኤ ላይ የሚከተሉት አካላት የሂደቱ ቁልፍ ከዋኞች ሆነው በሂደቱ ተሳትፎ እያደረጉ ይገኛሉ፡፡

1. ተሳታፊዎች
ተሳታፊዎች የሀገራዊ ምክክር ሂደቱ ዋና አካል ናቸው። ከተሳታፊዎች የሚከተሉት ይጠበቃሉ፦
👉በንቃት እና የምክክር ሂደቱን በሚደግፍ መልኩ መሳተፍ፤
👉አመለካከታቸውን በነፃነት እና በአክብሮት ማጋራት፤
👉ሌሎችን በጥንቃቄ ማዳመጥ፤
👉ለጋራ መፍትሔዎች አብሮ በጋራ መስራት።

በጉባኤው ላይ እነማን ይሳተፋሉ?
👉የየወረዳው የሕብረተሰብ ክፍል ወኪሎች
👉የክልል/ከተማ አስተዳደር ባለድርሻ አካላት ወኪሎች
👉የፌዴራል ባለድርሻ አካላት ወኪሎች እና
👉የዲያስፖራው ማህበረሰብ ወኪሎች ተሳትፎ በማድረግ ላይ ይገኛሉ

2. ኮሚሽኑ
👉የገለልተኛ መሪነት ሚናን በመጫወት የምክክር ሂደቱን በበላይነት ይቆጣጠራል፤
👉የምክክር ሂደቶቹ ከኮሚሽኑ ተልዕኮ ጋር መጣጣማቸውን ያረጋግጣል፤
👉ለምክክር ሂደቱ ነፃና ምቹ አካባቢን ይፈጥራል፤
👉ለምክክር ሂደቱ አስተዳደራዊና ቴክኒካዊ መመሪያ ይሰጣል፡፡

3. አመካካሪዎች
👉የምክክር ሂደቶች ከአድልዎ ነፃ በሆነ እና ሙያዊ በሆነ መንገድ ይመራሉ፤
👉አክብሮት የተሞላበት እና ሁሉንም ያካተተ ተሳትፎን ያበረታታሉ፤
👉የምክክር ሂደቶቹ በአጀንዳው ነጥቦች ላይ ብቻ እንዲያተኩሩ ያደርጋሉ፤
👉የሃሳብ መስጫ ጊዜን በፍትሐዊነት ያስተዳድራሉ፡፡

4. ቴክኒካዊ ባለሙያዎች (የባለሙያዎች ቡድን) (Panel of Experts)
👉በአጀንዳ ነጥቦች ላይ ለሚፈጠሩ ብዥታዎች እና ማብራሪያዎች ተጨማሪ ማብራሪያ ይሰጣሉ፤
👉ተገቢ የሆኑ ምርምሮችን እና ማስረጃዎችን በመጥቀስ የምክክር ሂደቱን የሚደግፉ ሃሳቦችን ያቀርባሉ፡፡

5. ታዛቢዎች
👉ታዛቢዎች የምክክር ሂደቱን አሳታፊነት፣ አካታችነት ወዘተ በተለያዩ መመዘኛዎች በገለልተኝነት ይከታተላሉ። የእነሱ መገኘት ለምክክሩ ግልጽነት እና ተዓማኒነት አስተዋጽኦ ያደርጋል።

6. ሽማግሌዎች
👉ሽምግሌዎች በየትኛውም የምክክር ምዕራፍ በተለያዩ የምክክሩ ተሳታፊ አካላት መካከል ጥልቅ አለመተማመን፣ የማይታረቁ ፍላጎቶች ወይም ሁከት በሚያጋጥሙበት ጊዜ ወደ መግባባት መንገድ እንዲመጡ እገዛ ያደርጋሉ፡፡ በተለይ ተሳታፊዎቹ ባለመግባባታቸው ምክንያት የምክክር ሂደቱ ሲቋረጥ ወይም ቅርቃር (deadlock) ውስጥ ሲገባ ሽምግልና (mediation) ተግባራዊ ይሆናል፡፡

#ኢትዮጵያ_እየመከረች_ነው #ኢትዮጵያ #አሚኮ

#ባሕር_ዳር #ሐምሌ10/2018 ዓ.ም

Previous articleበክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎት ለ20 ሚሊዮን ዜጎች ነጻ የጤና አገልግሎት ሊሰጥ ነው።
Next article‘ሁሉም የተሳተፉበት፣ ያለ ልዩነት የተካተቱበት‌”