
የኦሮሞ ብሔረሰብ አሥተዳደር ምክር ቤት 5ኛ ዙር 28ኛ መደበኛ ጉባኤውን አካሂዷል።
በጉባኤው በ2018 የተሠሩ የሰላም፣ የልማት እና የመልካም አሥተዳደር ሥራዎች በምክር ቤቱ አባላት ተገምግመዋል።
የኦሮሞ ብሔረሰብ አሥተዳደር ምክር ቤት ዋና አፈጉባኤ ፋጡማ ሞላ በ2018 በጀት ዓመት በሰላም ግንባታ የተሠራው ሥራ አበረታች ነው ብለዋል።
ከአጎራባች ወንድም ሕዝቦች ጋር የተጀመረው የሕዝብ ለሕዝብ ግንኙነትም ጠንካራ እንዲኾን የተሠራበት ዓመት መኾኑን ገልጸዋል።
የኦሮሞ ብሔረሰብ አሥተዳደር ዋና አሥተዳዳሪ አህመድ አሊ በ2018 በጀት ዓመት ዘላቂ ሰላም ለመገንባት በተሠራው ሥራ በርካታ የታጠቁ አካላት ወደ ሰላም እንዲመጡ መደረጉን አስረድተዋል።
የሕዝቡን የልማት ጥያቄዎች ለመመለስም በርካታ ፕሮጀክቶች የተገነቡበት ዓመት መኾኑንም ዋና አሥተዳዳሪው አክለዋል።
በ2019 በጀት ዘላቂ ሰላምን በመገንባት ልማትን ለማረጋገጥ በምክር ቤቱ መግባባት መፈጠሩንም ተናግረዋል።
የብሔረሰብ አሥተዳደሩ የምክር ቤት አባላት በበኩላቸው ግብርናን በማዘመን የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ የተሠራው ሥራ አበረታች እንደነበር ጠቅሰዋል።
የምክር ቤቱ አባላት በቋሚ ኮሚቴዎች በኩል በየጊዜው ድጋፍ እና ክትትል ሲያደርጉ እንደነበርም አብራርተዋል።
#ከሚሴ፡ ሐምሌ 9/2018 ዓ.ም
ዘጋቢ:- ይማም ኢብራሒም
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
