
የአማራ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የፍርድ ቤቶችን የ2018 በጀት ዓመት እና የባለፉትን ሦሥት ዓመታት የትራንስፎርሜሽን ዕቅድ አፈጻጸም እየገመገመ ነው።
ፍርድ ቤቶች ሕግን እና ማስረጃን መሠረት በማድረግ ለዜጎች የንብረት፣ የፈጠራ፣ የሰብዓዊ መብት እና ደኅንነት መከበር ለሀገር ዕድገት መሠረታዊ የኾኑ ተቋማት መኾናቸውን ገልጸዋል።
የአማራ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤትም በሕገ መንግሥት እና በሌሎች ዝርዝር ሕጎች የተሰጠውን ኀላፊነት በአግባቡ ለመወጣት ትኩረት ሰጥቶ እየሠራ መኾኑን ጠቁመዋል።
ይህንንም እውን ለማድረግ ከ2016 ዓ.ም እስከ 2018 ዓ.ም ተግባራዊ የሚደረግ የዳኝነት እና የፍትሕ ትራንስፎርሜሽን ዕቅድ ተዘጋጅቶ ሢሠራ መቆየቱን ገልጸዋል።
ከዚህም የ2018 በጀት ዓመት ዕቅድን በማዘጋጀት፣ ልዩ ትኩረት የሚሻቸውን ሥራዎች በ100 ቀናት ዕቅድ ውስጥ በማካተት ሲተገብር ቆይቷል ነው ያሉት። በዚህም ተጨባጭ ለውጦች እና ውጤቶችን ማስመዝገብ እንደተቻለ አስታውቀዋል፡፡
የዳኝነት ነፃነት እና ገለልተኝነትን ከማረጋገጥ አንጻር ብዙ ተጨባጭ ሥራዎች መሠራታቸውንም ገልጸዋል፡፡፡
ለፍርድ ቤቱ ስኬት አስተዋጽኦ ላደረጉ በየደረጃው ላሉት የመንግሥት ተቋማት፣ አስፈጻሚዎች፣ ምክር ቤቶች፣ የፍትሕ ተቋማት ትብብር፣ የማስረጃ ሰጭዎች እና ሌሎች ባለድርሻ አካላት ምሥጋና አቅርበዋል።
#ባሕር_ዳር ሐምሌ 8/2018 ዓ.ም
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
