የኢትዮጵያ የኅብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ዘመናዊ ቴክኖሎጂን በመጠቀም የላቀ አገልግሎት እንዲሰጥ መሥራት ይገባል።

3

የኢትዮጵያ የኅብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት 100ኛ ዓመት የምሥረታ በዓሉን እያከበረ ነው።

በዓልሉ ላይ የተገኙት የኢፌዴሪ ፕሬዝዳንት ታዬ አጽቀሥላሴ እንደ ኢትዮጵያ ኅብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ያሉ ዘመን ተሻጋሪ ተቋማትን የበለጠ ለማሳደግ አስፈላጊውን ሥራ መሥራት ይገባል ብለዋል።

ተቋሙ ዘመናዊ ቴክኖሎጂን በመጠቀም የዲጅታል የጤና መረጃ አያያዝን ማሳደግ እና የላቀ አገልግሎት መስጠት እንዲች አስፈላጊውን ተግባር መሥራት እንደሚገባም ጠቁመዋል።

የተቋሙ መቶኛ ዓመት የሚዘከረው ለሚመጣው በሚገባ አቅዶ ለመሥራት ነው ያሉት ፕሬዝዳንቱ መንግሥት ለተቋሙ የሚሰጠውን ሙሉ ድጋፍ እንደሚቀጥልም ተናግረዋል።

#አሚኮ #የኢትዮጵያ_የኅብረተሰ_ጤና_ኢንስቲትዩት #ኢትዮጵያ🇪🇹
#አዲስ_አበባ፡ ሐምሌ 9/2018 ዓ.ም
ዘጋቢ: አየለ መስፍን
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!

Previous article🇪🇹 “ልዩነት ውስጥ ያለ ውበት፤ በውይይት የታጀበ የፖለቲካ ባሕል ለነገዋ ኢትዮጵያ”
Next article“የዳኝነት እና የፍትሕ ሥርዓት ግንባታዎች ለሀገር ዕድገት የላቀ ድርሻ አላቸው” አቶ አለምዓንተ አግደው