
የሀረሪ ክልል ምክር ቤት 6ኛ ዙር 5ኛ ዓመት 10ኛ መደበኛ ጉባኤውን ማካሄድ ጀምሯል።
ምክር ቤቱ ለሁለት ቀናት በሚያካሄደው ጉባኤ በተለያዩ አጀንዳዎች ዙሪያ ይመክራል።
የክልሉ መሥተዳድር ምክር ቤት የ2018 በጀት ዓመት የሥራ አፈጻጸም ሪፖርት በክልሉ ርእሰ መሥተዳድር ኦርዲን በድሪ ቀርቦ ውይይት ከተደረገበት በኃላ ይጸድቃል ተብሎ ይጠበቃል።
የክልሉ ምክር ቤት ጽሕፈት ቤት ፣ የጠቅላይ ፍርድ ቤት እና ዋና ኦዲተር መሥሪያ ቤት የ2018 በጀት ዓመት የሥራ አፈጻጸም ሪፖርት በመገምገም እንደሚያጸድቅ ተገልጿል።
ከዚህ በተጨማሪም የክልሉ መንግሥት የ2019 በጀት ዓመት ረቂቅ በጀት እና የ2019 በጀት ዓመት እቅድ ለምክር ቤቱ ቀርቦ ይጸድቃል ተብሏል። ምክር ቤቱ ለሁለት ቀናት በሚያካሂደው ጉባኤ የተለያዩ አዋጆችን እና ሹመቶችን እንደሚያጸድቅም ተመላክቷል።
#ሀረሪክልል#ምክርቤት
#ባሕር_ዳር፡ሐምሌ 9/2018 ዓ.ም
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
