በኢትዮጵያ የአሜሪካ አምባሳደር ኤርቪን ማሲንጋ ጎንደር ገቡ።

5


በኢትዮጵያ የአሜሪካ አምባሳደር ኤርቪን ማሲንጋ የሚመራ የልዑክ ቡድን ጎንደር ከተማ ገብቷል።

የልዑክ ቡድኑ ጎንደር አፄ ቴዎድሮስ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርስ የአማራ ክልል ከተማ እና መሠረተ ልማት ቢሮ ኀላፊ ሞላ መልካሙ ( ዶ.ር) የጎንደር ከተማ አሥተዳደር ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ ቻላቸው ዳኘው፣ የጎንደር ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት አሥራት አጸደወይን ጨምሮ ሌሎች የሥራ ኀላፊዎች አቀባበል አድርገውላቸዋል።

የአሜሪካ አምባሳደር ኤርቪን ጄ. ማሲንጋ የንግድ ዲፕሎማሲን ለማስፋፋት፣ የሰላምና የመረጋጋትን አስፈላጊነት ለማጉላት እና የአሜሪካ የውጭ እርዳታ ሊለካ የሚችል ውጤት እንዲያመጣ ለማረጋገጥ ያለመ ጉዞ ማድረጋቸው ተጠቁሟል።

አምባሳደር ኤርቪን ማሲንጋ በጎንደር ከተማ ቆይታቸው ከከተማ አሥተዳደሩ የሥራ ኀላፊዎች ጋር በተለያዩ ጉዳዮች ዙሪያ ይወያያሉ።

የልዑክ ቡድኑ የጎንደር ዩኒቨርሲቲ እየሰራቸው ያሉ ተግባራትን እና የፋሲል የጎንደር አብያተ መንግሥታት ታሪካዊ ቦታዎች ይጎበኛሉ ተብሎ ይጠበቃል።

ዘጋቢ:- ኀይሉ ማሞ
#ባሕር_ዳር፡ ሐምሌ 9/2018 ዓ.ም

Previous articleዘመናዊ ግብርናን እውን ለማድረግ መሬትን መንከባከብ ያስፈልጋል።
Next articleየሀረሪ ክልል ምክር ቤት መደበኛ ጉባኤውን ማካሄድ ጀመረ።