ከአንዲት ማይክሮስኮፕ እስከ ዘመናዊ የምርምር ማዕከል።

5
​የኢትዮጵያ ሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት የመቶኛ ዓመት የምስረታ በዓሉን እና 5ኛውን የሕብረተሰብ ጤና ሳይንሳዊ ጉባኤ ሊያከብር ነው።
የኢንስቲትዩቱ ዋና ዳይሬክተር ዶክተር መሳይ ኃይሉ ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ፣ ተቋሙ ዛሬ ላይ ለደረሰበት ታላቅ ደረጃ ለመብቃት ባለፉት 100 ዓመታት ውስጥ በርካታ ውጣ ውረዶችንና መዋቅራዊ ለውጦችን ማለፉን ገልጸዋል።
🔬 ከሩሲያ ቀይ መስቀል እስከ አሁኑ የሕክምና ማዕከል ​የኢንስቲትዩቱ ታሪክ የጀመረው በሩሲያ ቀይ መስቀል የጤና ባለሙያዎች አማካኝነት ዘመናዊ የላብራቶሪ አገልግሎት በመጀመር ነበር። በጥቂት ባለሙያዎች እና በአንዲት ማይክሮስኮፕ ስራውን የጀመረው ተቋሙ፣ በሂደት፦
👉የኢፔርያል ኢንስቲትዩት፣
👉የፓስተር የምርምር ተቋም እና
👉የተላላፊ በሽታ ምርምር ተቋም በመሆን ሀገራዊ የክትባት መድኃኒቶችን እያመረተ ማገልገሉን አስታውሰዋል።
👉በ2006 ዓ.ም ደግሞ በአዲስ መዋቅር “የኢትዮጵያ የኅብረተሰብ ጤና ኢንስትትዩት” ተብሎ ስሙ ተቀይሮ የሕዝብን የጤና ስጋቶች በመቅረፍ ላይ ይገኛል።
🌍 በሀገር ውስጥ አቅም ታሪክ መስራት! ​ኢንስቲትዩቱ አሁን ላይ በደረሰበት ዘመናዊ የላብራቶሪ ብቃት፣ እንደ ማርበርግ እና የዝንጀሮ ፈንጣጣ (Mpox) ያሉ አስፈሪ በሽታዎችን ሙሉ በሙሉ በሀገር ውስጥ አቅም መመርመር መለየት መቻሉ ተገልጿል። በተጨማሪም፦
👉ባለፈው ዓመት ብቻ ከ7 ሚሊዮን በላይ ተጓዦችን የጉዞ ሥርዓት በመከታተል ተላላፊ በሽታዎች ወደ ሀገር እንዳይገቡና እንዳይስፋፉ መከላከል ተችሏል።
👉ከወረዳ እስከ ሀገር አቀፍ ደረጃ ፈጣን መረጃዎችን በመሰብሰብ ለጤና ስጋቶች አፋጣኝ ምላሽ የሚሰጥበት ጠንካራ የቅኝት ሥርዓት ተዘርግቷል።
🎉 ታላቁ በዓል እንዴት ይከበራል? ​ይህ ታሪካዊ የመቶኛ ዓመት በዓል ከፊታችን ሐምሌ 09/2018 ዓ.ም ጀምሮ ለተከታታይ ሦስት ቀናት ይከበራል። በበዓሉ ላይ ታዋቂ ሳይንቲስቶች፣ የጤና ምሁራንና ባለድርሻ አካላት የሚሳተፉ ሲሆን፣ የላቁ የምርምር ሥራዎችና የተቋሙን የወደፊት የ100 ዓመታት ጉዞ የሚያመላክቱ ሳይንሳዊ ጽሑፎች ቀርበው ውይይት እንደሚደረግባቸው ተገልጿል።
#ባሕር_ዳር፡ ሐምሌ 07/2018 ዓ.ም
📲 ለተጨማሪ ፈጣንና ትኩስ መረጃዎች ገጻችንን Like እና Follow በማድረግ ይከተሉ!
ዘጋቢ: አየለ መስፍን
Previous articleጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር) ከኦሊሴጉ ኦባሳንጆ ጋር ተወያዩ።
Next articleሴቶች ሰላም ፈጣሪ እና የሰላም መሪ ሊኾኑ ይገባል።