ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር) ከኦሊሴጉ ኦባሳንጆ ጋር ተወያዩ።

8

 

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር) ከኦሊሴጉ ኦባሳንጆ ጋር ተወያይተዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክት ዛሬ በታሪካዊው የሀገራዊ ምክክራችን ዋዜማ፣ የኢትዮጵያ ታላቅ ወዳጅ የኾኑትን ኦሊሴጉን ኦባሳንጆን በጽሕፈት ቤቴ ተቀብያለሁ ብለዋል።

በመጪው ሀገራዊ ምክክር ዙሪያ ለመወያየት፣ ከዚህ ቀደም ካከናወኗቸው ተግባራት ጥበብ ለመቅሰም ችለናል፤ በተለይም የቢያፍራን የሰላም ሂደት በመምራት ያካበቱትን ልምድ አጋርተውናል ነው ያሉት። ይህም ኢትዮጵያ በምክክር ለምታረጋግጠው አንድነት እና ዘላቂ የሰላም ጉዞ ላይ ትልቅ ትምህርት የሚሰጥ ነው ብለዋል።

ኢትዮጵያ ለምታበረክቱት በዋጋ የማይተመን አስተዋጽኦ ሁልጊዜም የላቀ ምስጋናዋን ታቀርባለች ነው ያሉት በመልዕክታቸው።

#ባሕር_ዳር #ሐምሌ_07_2018_ዓ_ም

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!

Previous articleየከተሞች የለውጥ ጉዞ፤ የኮሪደር ልማት እና የአርሶ አደሮች የዘመናዊ ሕይወት ጅማሮ