
ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክት የደብረ ማርቆስ ንጉሥ ተክለ ሃይማኖት አውሮፕላን ማረፊያ ዛሬ ተመርቋል ብለዋል።
ደበረ ማርቆስ ከ60 ዓመታት በፊት አውሮፕላን ማረፊያ ነበራት፤ ለዘመናት ካገለገለ በኋላ እንዲቀር ተደረገ፤ ሕዝቡም በተደጋጋሚ ሲጠይቅ ኖረ ነው ያሉት።
የለውጡ መንግሥት ይሄንን የሕዝቡን ጥያቄ መልሷል። ጥያቄው የተመለሰው በሕዝብ ስለተጠየቀ ብቻ አይደለም። ትክክለኛ ስለሆነ እንጂ ብለዋል።
የአውሮፕላን ትራንስፖርት አገልግሎት መጀመር የአካባቢውን ቱሪዝም እና ንግድ የበለጠ ያሣልጠዋል ተብሎ እንደሚጠበቅ ገልጸዋል።
የመደመር መንግሥት ኢትዮጵያን በመሠረተ ልማት ማስተሣሠርና ኅብረ ብሔራዊ አንድነትን መገንባት ተልዕኮው ነው። ይሄንንም በሌሎችም የሀገሪቱ አካባቢዎች አጠናክሮ ይቀጥላል ነው ያሉት።
#ባሕር_ዳር ሐምሌ05_2018_ዓ_ም
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
