
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር) በደብረ ማርቆስ ከተማ ችግኝ ተክለዋል። ከጠቅላይ ሚኒስትሩ በተጨማሪ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ፣ የአማራ ክልል ርእሰ መሥተዳድር አረጋ ከበደ እና ሌሎች ከፍተኛ የሥራ ኀላፊዎችም ችግኝ ተክለዋል።
የደብረ ማርቆስ ንጉሥ ተክለሃይማኖት አውሮፕላን ማረፊያን የመረቁት ጠቅላይ ሚኒስትሩ የአረንጓዴ አሻራቸውንም አሳርፈዋል።
በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ( ዶ.ር) የተጀመረው የአረንጓዴ አሻራ ኢትዮጵያን አረንጓዴ እያለበሰ፣ የቀደም ገጽታዋን እየመለሰ እና የደን ሃብቷን እያሳደገ ነው። ጠቅላይ ሚኒስትሩ የልማት ሥራዎችን በሚመረቁበት እና በሚጎበኙት ጊዜ የአረንጓዴ አሻራቸውን ያሳርፋሉ። ዛሬም በደብረ ማርቆስ ከተማ አረንጓዴ አሻራቸውን አሳርፈዋል።
#አሚኮ_ዜና #DebreMarkosAirport #ንጉሥተክለሃይማኖትአውሮፕላንማረፊያ #EthiopiaAviation
#ባሕር ዳር:ሐምሌ 05/2018 ዓ.ም
ዘጋቢ:- ታርቆ ክንዴ
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
