
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር) የደብረ ማርቆስ ንጉሥ ተክለሃይማኖት አውሮፕላን ማረፊያን መርቀው ሥራ አስጀምረዋል።
በማስጀመሪያ ሥነ ሥርዓቱ ከጠቅላይ ሚኒስትሩ በተጨማሪ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ፣ የአማራ ክልል ርእሰ መሥተዳድር አረጋ ከበደ እና ሌሎች ከፍተኛ የሥራ ኀላፊዎች ተገኝተዋል።
የደብረ ማርቆስ ንጉሥ ተክለሃይማኖት አውሮፕላን ማረፊያ የዓመታት የሕዝብ ጥያቄ የነበረ ነው። አሁን ላይ ጥያቄው ምላሽ አግኝቶ አውሮፕላን ማረፊያው ተጠናቆ ሥራ ጀምሯል። በቀን ሦስት በረራዎችን በሳምንት 21 በረራዎችን ያደርጋል ነው የተባለው።
አውሮፕላን ማረፊያው ቦይንግን ጨምሮ ታላላቅ አውሮፕላኖችን ማሰረፍ የሚችል እና ለአካባቢው ኢንቨስትመንት መነቃቃት ትልቅ አስተዋጽኦ የሚያደርግ ነው።።
#DebreMarqos #Ethiopia #Infrastructure #Aviation #PMAbiyAhmed
#ባሕር_ዳር፡ ሐምሌ 05/2018 ዓ.ም
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
ዘጋቢ:- ታርቆ ክንዴ
