“ኢትዮጵያ እየመከረች ነው” የ5 ኪሎ ሜትር የጎዳና ላይ ሩጫ ተካሄደ።

6

 

የኢትዮጵያ ሀገራዊ የምክክር ኮሚሽን ባዘጋጀው የ5 ኪሎ ሜትር የጎዳና ላይ ሩጫው በርካታ የማኅበረሰብ ክፍሎች ተሳታፊ በኾኑበት ነው በአዲስ አበባ ከተማ የተካሄደው።

የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ከሐምሌ 8/2018 ዓ.ም ጀምሮ ለሚያካሄደው ሀገራዊ የምክክር ጉባኤ ግንዛቤ መፍጠር ደግሞ የሕዝባዊ ሩጫው ዋና አላማ ነው ተብሏል።

የኢትዮጵያ ሀገራዊ የምክክር ኮሚሽን ባለፉት አራት ዓመታት በርካታ ተግባራትን ሲያከናውን መቆየቱን የተናገሩት የኮሚሽኑ ዋና ኮሚሽነር ፕሮፌሰር መሥፍን አርዓያ ናቸው።

ለመጨረሻው የምክክር ጉባኤ ከመላው ሀገሪቱ የተውጣጡ
4 ሺህ የሚኾኑ ተመካካሪዎች ከሀምሌ 8/2018 ዓ.ም ጀምሮ በስምንት አጀንዳዎች ላይ ይመክራሉ ብለዋል።

እንደ ሀገር የማያግባቡ አጀንዳዎች በምክክር ጉባኤው ተመክሮባቸው ወደ ስምምነት እንደሚመጣም ያላቸውን ተስፋ ገልጸዋል።

ዛሬ የተካሄደው የ5 ኪሎ ሜትር የጎዳና ላይ ሕዝባዊ ሩጫ ከጥቂት ቀናት በኋላ ለሚካሄደው የምክክር ጉባኤ መነቃቃትን እና ግንዛቤን ለመፍጠር እንደተዘገጀ ዋና ኮሚሽነሩ ፕሮፌሰር መስፍን አርዓያ ተናግረዋል።

#EthiopiaNationalDialogueCommission
#ሀገራዊ_ምክክር
#ሕዝባዊሩጫ #ሐምሌ5_2018_ዓ_ም

ዘጋቢ፦ ባዘዘው መኮንን

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!

Previous articleየዋግ ኽምራን የመብራት መቆራረጥ ለመቅረፍ የኮንክሪት ምሰሶዎች ሊሠሩ ነው።