
በጉብኝቱ ከርእሰ መሥተዳድር አረጋ ከበደ በተጨማሪ የአማራ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዝዳንት ዓለምአንተ አግደው፤ የአማራ ክልል ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት ኀላፊ ይረጋ ሲሳይ እና ሌሎች ከፍተኛ የሥራ ኀላፊዎችም ተገኝተዋል።
የአማራ ልማት ማኅበር (አልማ) በደብረ ማርቆስ ከተማ እያስገነባው የሚገኘውን ባለ 10 ወለል ሕንጻን፤ የደብረ ማርቆስ ጠቅላላ ሆስፒታል ፕሮጀክትን፤ የደብረ ማርቆስ ከተማ መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት ፕሮጀክትን፤ በአማራ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የምሥራቅ ጎጃም ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት የሥራ እንቅስቃሴን እና የከተማዋ የኮሪደር ልማት በከፍተኛ መሪዎች ተጎብኝተዋል።
ደብረ ማርቆስ ከተማ ሰላሟን እየጠበቀች በርካታ የልማት ሥራዎችን እየሠራች ነው። የልማት ሥራዎቹ የነዋሪዎቿን አኗኗር የሚቀይሩ እና የከተማዋን እድገት የሚያፋጥኑ ናቸው።
#አማራ_ክልል #ደብረ_ማርቆስ #የልማት_ሥራዎች #የኮሪደር_ልማት #አማራ_ልማት_ማኅበር #አልማ #አሚኮ #ደብረ_ማርቆስ #ሐምሌ4_2018_ዓ_ም
ዘጋቢ:- ታርቆ ክንዴ
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
