የፌዴራል ፖሊስ ለሜቄዶኒያ ማዕከል የ2 ሚሊዮን ብር እና የአምቡላንስ ድጋፍ አደረገ።

10

 

የኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ ከፍተኛ ኀላፊዎች የሜቄዶኒያን የሆስፒታል ግንባታ፤ በማዕከሉ የሚረዱ አረጋውያንን እና የአዕምሮ ህሙማንን ጎብኝተዋል።

ማዕከሉ በአሁኑ ሰዓት ለ9 ሺህ ሰዎች አገልግሎት እየሰጠ ይገኛል።

የኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ ጠቅላይ አዛዥ ኮሚሽነር ጄኔራል ደመላሽ ገብረ ሚካኤል ፤ የፖሊስ ሥራ የኅብረተሰቡን ሰላም እና ደኅንነት መጠበቅ እና መታደግ ነው ብለዋል።

ተቋሙ ላለፉት ሦስት ዓመታት ሐምሌ 4 የፖሊስ ቀን ኾኖ እንዲታሰብ በመወሰን በመቄዶኒያ የአረጋውያን እና የአዕምሮ ህሙማን መርጃ ማዕከል ያሉ ወገኖችን በመጎብኝት እያሳለፉ እንደሚገኙ ገልጸዋል።

የፌዴራል ፖሊስ ለማዕከሉ 2 ሚሊዮን ብር እና አንድ አምቡላንስ ተሽከርካሪ ድጋፍ አድርጓል ነው ያሉት።

በቀጣይ ዓመት ደግሞ ሐምሌ አራትን በሌላ አካባቢ በሚገኘው የማዕከሉ መርጃ ማዕከል እንደሚያከብሩም ጠቁመዋል።

የመቄዶኒያ የአረጋውያን እና የአዕምሮ ህሙማን መርጃ ማዕከል መሥራች እና ሥራ አሥኪያጅ ክቡር ዶክተር ቢኒያም በለጠ የፌዴራል ፖሊስ በየዓመቱ የሚያደረገው ድጋፍ እና ትብብር ቀላል አይደለም ብለዋል።

ማዕከሉ በየቀኑ የሚያወጣው ወጪ ትልቅ ነው፤ ይህን በማድረጋችሁ ዋጋችሁ ብዙ ነው ሲሉም ገልጸዋል።

የመቄዶኒያ የአረጋውያ መረጃ ማዕከል እንደዚህ ባለው በጎ ድጋፍ የቆመ ነው፤ ለተደረገው በጎ ነገር ሁሉ እናመሰግናለን ብለዋል።

ለመርጃ ማዕከሉ ማስፋፊያ እና ለሆስፒታል ግንባታ ማጠናቀቂያ ይሆን ዘንድ ተቋማት ድጋፍ እና እገዛ እንዲያደርጉም ጥሪ አቅርበዋል።

#ኢትዮጵያ_ፌደራል_ፖሊስ #ሜቄዶኒያ #በጎ_አድራጎት #ሰብአዊ_ድጋፍ #አዲስ_አበባ #አሚኮ #EthiopianFederalPolice
#አዲስ_አበባ #ሐምሌ4_2018_ዓ_ም

ዘጋቢ፦ አየለ መስፍን

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!

Previous articleለሀገራዊ ጉባኤ ተመካካሪዎች የቅድመ ምክክር ገለጻ እየተሰጠ ነው፡፡
Next article📣 የጠራ እና ግልጽ የመረጃ ፍሰት ሀገርን በምክክር ለማሻገር የሚኖረው ወሳኝነት 🕊️