ለሀገራዊ ጉባኤ ተመካካሪዎች የቅድመ ምክክር ገለጻ እየተሰጠ ነው፡፡

6

 

የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ከሐምሌ 8/2018 ዓ.ም ጀምሮ በሚያካሄደው ሀገራዊ የምክክር ጉባኤ ለሚሳተፉ ተመካካሪዎች የቅድመ ምክክር ገለጻ መስጠት ጀምሯል።

ዋና ኮሚሽነር ፕሮፌሰር መሥፍን አርአያ፤ ኢትዮጵያ ለአፍሪካ ነፃነት ተምሳሌት መኾኗን ገልጸዋል።

ሁላችንም ኢትዮጵያዊያን የአድዋን መንፈስ ሰንቀን ለሀገር ግንባታ ያዳበርነውን ወደ ምክክር እና መግባባት መቀየር ያስፈልገናልም ብለዋል።

በሚቀጥሉት ሦስት ቀና የሚሰጠውን ገለጻ በአንክሮ በመከታተል ምክክሩን በስኬት ማከናወን እንደሚገባም አሳስበዋል።

በገለጻው ወቅት የሀገራዊ ምክክር ጉባኤው ዓላማ፣ የውይይት ሂደት፣ የተመካካሪዎች ሚናና ኃላፊነት፣ እንዲሁም የውይይቱን ሥነ ምግባርና የአሠራር ሥርዓት በተመለከተ ማብራሪያ እየተሰጠ ነው።

ገለጻው ተመካካሪዎች በቂ ግንዛቤ እንዲኖራቸውና በሀገራዊ የምክክር ጉባኤው ውጤታማ ተሳትፎ እንዲያደርጉ ለማስቻል መዘጋጀቱም ተገልጿል።

በገለጻው ላይ ከመላው ኢትዮጵያ የተወጣጡ ተመካካሪዎች ተገኝተዋል።

#ሀገራዊምክክር #አዲስአበባ #አሚኮ #ኢትዮጵያ

#ባሕር_ዳር ሐምሌ 4/2018 ዓ.ም

Previous article14 የበጎ ፈቃድ ተግባራት እና የማኅበራዊ ትስስር ፋይዳ በሐረሪ ክልል !