
የክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎት አቅመ ደካሞችን ከመደገፍ ባሻገር በሕዝቦች መካከል ጠንካራ ማኅበራዊ ትስስርን የመፍጠር ፋይዳው የጎላ ነው።
በብልጽግና ፓርቲ የሐረሪ ክልል ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት ኀላፊ ጌቱ ወዬሳ የዘንድሮውን የክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎት በሚመለከት መግለጫ ሰጥተዋል።
የክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎት አቅመ ደካሞችን ከመደገፍ ባለፈ በሕዝቦች መካከል ጠንካራ ማኅበራዊ ትስስርን የመፍጠር ትልቅ ፋይዳ ያለው መኾኑን ገልጸዋል።
በዘንድሮ የክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎት 14 የተለያዩ በጎ ፈቃድ ተግባራቶች ታቅደው ወደ ሥራ መገባቱን ተናግረዋል።
የክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎት በዋናነት የአቅመ ደካማ እና የእጅ አጠር ወገኖችን ቤት የመጠገን፣ የማደስ እና አዳዲስ የመኖሪያ ቤቶችን የመገንባት ሥራዎችን ያካትታል ብለዋል።
ሀገር በቀል እና የፍራፍሬ ችግኞችን በመትከል የአካባቢ ጥበቃ እና የእርሻ ሥራዎች በትኩረት እንደሚከናወኑም ነው የገለጹት።
በሕዝብ አቅም እና አጋር አካላትን በማሥተባበር አዲስ የመማሪያ ክፍሎች ግንባታ እና የነባር የመማሪያ ክፍሎችን እድሳት እንደሚከናወን ገልጸዋል።
የትምህርት ቁሳቁስ ድጋፍ፣ የማዕድ ማጋራትን ጨምሮ ነጻ የምርመራ እና የህክምና አገልግሎትና የደም ልገሳ መርሐ ግብር ይካሄዳል ብለዋል።
ከተማውን ምቹ እና ለኑሮ ተስማሚ እንዲኾን የሚያስችሉ የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ሥራዎች እንደሚከናወኑ ኀላፊው ገልጸዋል።
በዚህ የክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎት መርሐ ግብር ከ344 ሺህ 614 የተለያዩ የኅብረተሰብ ከፍሎችን ተጠቃሚ ለማድረግ ታቅዶ ወደ ሥራ መገባቱንም ተናግረዋል።
#የክረምትበጎፈቃድ #ሐረሪክልል #ማህበራዊትስስር #አቅመደካሞችንመደገፍ
#Harar
#ባሕር_ዳር #ሐምሌ4_2018_ዓ_ም
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
