
ከርእሰ መሥተዳድሩ በተጨማሪ የአማራ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዝዳንት ዓለምአንተ አግደው፤ የአማራ ክልል ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት ኀላፊ ይረጋ ሲሳይ እና ሌሎች ከፍተኛ የሥራ ኀላፊዎችም ደብረ ማርቆስ ከተማ ገብተዋል።
ርእሰ መሥተዳድር አረጋ ከበደ እና ሌሎች ከፍተኛ የሥራ ኀላፊዎች ደብረ ማርቆስ ከተማ አዲሱ የንጉሥ ተክለሃይማኖት አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ የደብረ ማርቆስ ከተማ አሥተዳደር ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ ተሾመ ዋለ፤ የምሥራቅ ጎጃም ዞን ዋና አሥተዳዳሪ ኑርልኝ ብርሃኑን እና ሌሎች ከፍተኛ የሥራ ኀላፊዎች እና የከተማዋ ነዋሪዎች ደማቅ አቀባበል አድርገውላቸዋል።
ርእሰ መሥተዳድሩ በደብረ ማርቆስ ከተማ በሚኖራቸው ቆይታ የተሠሩ የልማት ሥራዎችን መርቀው አገልግሎት ያስጀምራሉ። በግንባታ ላይ የሚገኙ የልማት ሥራዎችንም ይጎበኛሉ።
ደብረ ማርቆስ ከተማ ሰላሟን እየጠበቀች የከተማዋን እድገት የሚያፋጥኑ የልማት ሥራዎችን እየሠራች ነው።
#ደብረ_ማርቆስ #ሐምሌ4_2018_ዓ_ም
ዘጋቢ:- ታርቆ ክንዴ
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
