
በደቡብ ጎንደር ዞን በእስቴ ወረዳ መካነ ኢየሱስ ከተማ ዙሪያ ሕግ ማስከበር ግዳጅ እየፈጸሙ የሚገኙ የኮር መሪዎች፣ የሠራዊት አባላት፣ የእስቴ ወረዳ የሥራ ኀላፊዎች እና የከተማው ማኅበረሰብ በከተማው ዙሪያ በሚገኙ ተራራዎች ላይ “ተስፋን እንትከል” በሚል መሪ መልእክት 10 ሺህ ችግኞችን በመትከል አረንጓዴ አሻራቸውን አሳርፈዋል።
በአካባቢው የሚንቀሳቀሰው ክፍለ ጦር ምክትል አዛዥ ሌተናል ኮሎኔል ጌትነት አግማስ የተካሄደው የችግኝ ተከላ መርሐ ግብር ወታደር ውጊያ ብቻ ሳይኾን የልማትም አርበኛ መኾኑን የሚያሳይ ነው ብለዋል።
የእስቴ ወረዳ ዋና አሥተዳደሪ ማንተፋርዶ ሞላ አረንጓዴ አሻራው ከሌላዉ ጊዜ ለየት የሚያደርገው የሠራዊት አባላት እና የከተማው ማኅበረሰብ በጋራ በመኾን ያከናወኑት በመኾኑ ነው ብለዋል። ዘገባዉ የምሥራቅ እዝ ነው።
#የምሥራቅእዝ #አረንጓዴአሻራ #እስቴወረዳ #ደቡብጎንደር #የኢፌዴሪመከላከያሠራዊት #የሕዝብናሠራዊትአንድነት
#ባሕር_ዳር፡ ሐምሌ 03/2018 ዓ.ም
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
